የወንዶች የዘር ፍሬ መጠን ከግማሽ በመቶ በላይ መቀነሱ ተገለጸ
ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ የወንዶች የዘር ፍሬ መጠን ከ101 ሚሊዮን ወደ 49 ሚሊዮን ዝቅ ማለቱን ተመራማሪዎች አስታውቀዋል
ፎስፌት የተሰኘው ኬሚካል ለወንዶች የዘር ፍሬ መጠን ማሽቆልቆል ዋነኛው ምክንያት ነው ተብሏል
የወንዶች የዘር ፍሬ መጠን ከግማሽ በመቶ በላይ መቀነሱ ተገለጸ።
እንደ ግሎባል ሄልዝ የጥናት ተቋም መረጃ ከሆነ የዓለማችን ወንዶች የዘር ፍሬ መጠን ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እያሽቆለቆለ መጥቷል።
በፈረንጆቹ 1973 ላይ በተደረገው ጥናት የአንድ ወንድ አማካኝ የዘር ፍሬ ወይም ስፐርም መጠን 101.2 ሚሊዮን ነበር።
በ1ሺህ 774 ሰዎች ላይ በተወሰደ ናሙና ይህ የወንዶች የዘር ፍሬ ወይም ስፐርም መጠን አሁን ላይ ወደ 49 ሚሊዮን ዝቅ ብሏል ተብሏል።
የወንዴ የዘር ፍሬ መጠን ከግማሽ በላይ መቀነሱ ቀስ በቀስ በሰው ልጆች ዘር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያመጣ እንደሚችልም የጣልያን እና አሜሪካ ተመራማሪዎች ይፋ ያደረጉት ጥናት ያስረዳል።
እንደ ተመራማሪዎቹ መረጃ ከሆነ ለወንዶች የዘር ፍሬ መጠን መቀነስ ዋነኛው ምክንያት በ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ከተባዮች ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚውለው ፎስፌት የተሰኘው ኬሚካል እንደሆነ ተገልጿል።
ኬሚካሉ ያለበትን አትክልት እና ፍራፍሬ የተመገበ ወንድ የዘር ፍሬው እንዲያመነጭ የሚያደርገውን ሆርሞን በመጉዳት የመጠን እንዲቀንስ ያደርጋልም ተብሏል።
ተመራማሪዎቹ አክለውም የሰው ልጆች ይክን ኬሚካል የተጠቀሙ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን ከመመገብ እንዲቆጠቡም መክረዋል።