ለ550 ልጆች አባት የሆነው ሆላንዳዊ የዘር ፍሬውን እንዳይለግስ ታገደ
ግለሰቡ የታገደው የዘር ፍሬውን የመለገስ ፍላጎቱ ባለመቆሙ ምክንያት ነው ተብሏል
የዘር ፍሬውን አግኝተው የተወለዱ ልጆች ግለሰቡ በፍርድ ቤት እንዲታገድላቸው ክስ መስርተው ነበር
ለ550 ልጆች አባት የሆነው ሆላንዳዊ የዘር ፍሬውን እንዳይለግስ ታገደ፡፡
በሀገረ ሆላንድ አንድ ግለሰብ የወንድ የዘር ፍሬውን በመለገስ የ550 ልጆች አባት መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በሀገሪቱ ህግ መሰረት አንድ ወንድ በፈቃደኝነት የዘር ፍሬውን መለገስ የሚችለው ለ12 ቤተሰቦች አልያም ለ25 ልጆች እንዲወለድ ቢልም ይህ ግለሰብ ግን ከዚያ በላይ ልጆች እንዲወለዱ ምክንያት ሆኗል ተብሏል፡፡
ይህ ግለሰብ በድብቅ እየዋሸ እና ተጨማሪ ሌሎች ድጋፎችን አደርጋለሁ እያለም ጭምር ለበርካታ የማዋለድ አገልግሎት ለሚሰጡ ኩባንያዎች የዘር ፍሬውን እንደሰጠ ተገልጿል፡፡
እንደዘባው ከሆነ ከዚህ በተጨማሪም ግለሰቡ ከሆላንድ ውጪ ባሉ ሀገራት ጭምር እና በበይነ መረብ በመታገዝ ቅስቀሳ በማድረግ የዘር ፍሬውን በመለገስ ብዙ ልጆች እንዲወለዱ ምክንያት ሆኗል።
በዚህ ምክንያትም ይህ ግለሰብ 550 ልጆች አባት ሆኗል የጠባለ ሲሆን ጉዳዩ በወላጆች እና በተወለዱ ህጻናት አዕምሮ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማድረሱ ተገልጿል፡፡
ይሁንና ይህ ግለሰብ አሁንም የዘር ፍሬውን የመለገስ እና የተጨማሪ ልጆች አባት የመሆን ፍላጎት እንዳለው መግለጹን ተከትሎ ጉዳዩ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል፡፡
በዚህ ግለሰብ የዘር ፍሬ የተጠቀሙ ወላጆች እና የተወለዱ ልጆች ጉዳዩን ይዘው ወደ ፍርድ ቤት ያመሩ ሲሆን የሀገሪቱ ፍርድ ቤትም ከእንግዲህ የዘር ፍሬ መለገስ እንዳይችል እገዳ ጥሎበታል፡፡
ከዚህ ግለሰብ የዘር ፍሬ የተቀበሉ የአዋላጅ ክሊኒኮች ካሉም የዘር ፍሬውን እንዳይጠቀሙ መወሰኑን በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ግለሰቡ እንደ ከዚህ በፊቱ የዘር ፍሬ ለመለገስ በበይነ መረብ ማስተዋወቅን እንዲያቆም እገዳ የተጣለበት ሲሆን ሀሰተኛ መረጃ በመጠቀም የዘር ፍሬውን የለገሳቸው አዋላጅ ክሊኒኮች ካሉም እንዲያሳውቅ ግዴታ ተጥሎበታል፡፡