የድንቅነሽ (ሉሲ) ቅጂ በዩኔስኮ ጽህፈት ቤት በቋሚነት ለዕይታ መቅረብ ጀመረ
ድንቅነሽ (ሉሲ) 3.2 ሚሊየን ዓመት ያላት የመጀመሪያዋ የሰው ልጅ ቅሪት አካል ነች
የሉሲ ቅጂ በፈረንሳይ ፓሪስ በሚገኘው የዩኔስኮ ዋና ጽህፈት ቤት በቋሚነት የሚቀመጥ ይሆናል
የድንቅነሽ (ሉሲ) ቅጂ በተባበሩት መንግሥታት የሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ዋና ጽህፈት ቤት በቋሚነት ለዕይታ መቅረብ ጀመረ።
የድንቅነሽ (ሉሲ) ቅጂ በዩኔስኮ ዋና ጽህፈት ቤት በቋሚነት የማስቀመጥ ስነ ስርዓት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ኦድሬ አዙሌ፣ እንዲሁም ፕሮፌሰር ድናልድ ጆሃንሰንና ኢቭ ኮፐንስ እና አምባሳደሮች በተገኙበት በፈረንሳይ ፓሪስ ተካሂዷል።
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዳ/ር ሂሩት ካሳው ሥነ ሥርዓቱን አስመልክቶ አስቀድሞ የተቀረፀ ንግግር መልእክት ማስተላለፋቸውንም በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ በፌስቡክ ገጻቸው አስታውቀዋል።
በሥነ-ሥረዓቱ አመርቂ በሆነ መልኩ ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት እንደሆነች ተንፀባርቋል ያሉት አምባሳደር ሄኖክ፤“ድንቅነሽ ዘር፣ ጎሳና ሀይማኖት ሳንለየ የጋራ ሰብአዊነታችን መገለጫ ናት” ብለዋል።
ድንቅነሽ (ሉሲ) 3.2 ሚሊዮን ዓመት ያላት የመጀመሪያዋ የሰው ቅሪት አካል ስትሆን በአፋር ውስጥ ሃዳር የተባለ ቦታ ኅዳር 24 ቀን 1974 ዓ.ም. መገኘቷ ይታወሳል።
የሉሲ ቅሪተ አካል የሚያሳየው በግዜው ቆማ ትሄድ እንደነበረ መሆኑንም ቂሩተ አካሉን ያገኙ ተመራማሪዎች ተናግረዋል።
ክክለኛው የድንቅነሽ (ሉሲ)ቅሪተ አካል በአዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ፖሊዎ አንትሮፖሎጂ ላብራቶሪ ውስጥ እንደሚገኝም ይታወቃል።