ማህሬዝ አውሮፖ ለሚጫወቱ ተመራጭ እየሆነ ወደመጣው የሳኡዲ አረቢያ ፕሮ ሊግ በቅርቡ የፈረመ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ቀጥሎ ትልቅ ስም ያለው ተጫዋች መሆን ችሏል
አልጀሪያዊው የማንቸስተር ሲቲ አጥቂ ማህሬዝ የሳኡዲ አረቢያውን አል-አህሊ ክለብ ተቀላቀለ።
ማህሬዝ ለሳኡዲው አል አህሊ ክለብ መፈረሙን ሮይተርስ የሳኡዲ መንግስት ሚዲያዎችን ጠቅሶ ዘግቧል።
ማህሬዝ አል-አህሊ በቅርብ ካስፈረማቸው ተጨዋቾች መካከል አንዱ መሆኑ ተገልጿል።
ማህሬዝ በ236 ጨዋታዎች ለሲቲ 78 ጎሎችን ያስቆጠረ እና 59 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አቀብሏል፤ በፈረንጆቹ 2018 ከሌስተር ሲቲ ከተዛወረ በኋላ አምስት የሊግ ሽልማቶችን ጨምሮ 11 ሽላማቶችን አግኝቷል።
ባለፈው የውድድር ዘመን በ47 ጨዋታዎች 15 ጎሎችን ያስቆጠረው የ32 አመቱ ማህሬዝ በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ሚናው ዝቅ ተደርጎ ተወስዶበታል።
ባለፈው አመት ለሲቲ እስከ 2025 የሚያቆየው ኮንትራት አድሶ ነበር።
ማህሬዝ አውሮፖ ለሚጫወቱ ተመራጭ እየሆነ ወደመጣው የሳኡዲ አረቢያ ፕሮ ሊግ በቅርቡ የፈረመ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ቀጥሎ ትልቅ ስም ያለው ተጫዋች መሆን ችሏል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ክበረወሰን በሰበረ ዋጋ ነበር የሳኡዲውን አል ናስር ክለብ የተቀላቀለው።
ለአንድ የውድድር ዘመን ሁለተኛ ዲቪዥን ውስጥ ያሳለፈው አል-አህሊ ወደ ሳኡዲ ፕሮ ሊግ ማደጉን ተከትሎ የሊቨርፑሉን ተከላካይ ተጨዋች ሮቤርቶ ፍርሚኖን እና የሴኔጋሉን ግብ ጠባቂ ኢድዋርድ መንዲን ለሶስት አመት በነጻ ዝውውር አስፈርሟል።