ሳዲዮ ማኔ፣ ሳላህና ማህሬዝን በድጋሚ ያካተተው የካፍ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች እጩ ዝርዝር ይፋ ሆነ
21 ጎሎችን ለሻምፒዮኑ አያክስ አምስተርዳም ያስቀጠረው ኮትዲቫራዊው አጥቂ ሰባስቲያን ሃለር ከእጩዎቹ አንዱ ነው ተብሏል
የካፍ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች የሽልማት ስነ ስርዓት ሃምሌ 21 ቀበሞሮኮ ራባት ይካሄዳል
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ፣ የግብጹ መሀመድ ሳላህ እና አልጄሪያዊው ሪያድ ማህሬዝ በድጋሚ የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች እጩ ዝርዝር ውስጥ ማካተቱን ይፋ አደረገ፡፡
ሶስቱ ተጫዋቾች ከ2016 ጀምሮ ፕሪሚየር ሽልማቱን በማሸነፍ ይታወቃሉ፡፡
የአመቱ ምርጥ ተጫዋች የነበረው ማኔ ከቀድሞ ክለቡ ሊቨርፑል ጋር ሁለት ዋንጫዎችን ለማንሳት የቻለ፤ ሴኔጋል በየካቲት ወር የአፍሪካ ዋንጫን እንድታነሳ እና ለፊፋ የዓለም ዋንጫ እንድታልፍ ትልቅ ሚና የነበረው ነው።
ማኔ በተጨማሪም የሴኔጋል የምንግዜም ኮከብ ግብ አግቢ በመሆን የሄንሪ ካማራን ሪከርድ ያሻሻለ ነው።
ሳላህ ከሊቨርፑል ጋር የብር ዋንጫን በማሸነፍ በፕሪምየር ሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ጨርሷል።
ሳላህ ምንም እንኳን በአፍሪካ ዋናጫ ባይሳካለትም፤ በፕሪሚየር ሊግ ኳስን አመቻችቶ በማቀበል የዓመቱ የላቀ ብቃት ያሳየ ተጫዋች ከመሆኑ በሻገር የእንግሊዝ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር የአመቱ ምርጥተጫዋች በመሆን ተመርጧል።
ሪያድ ማህሬዝ
በሌላ በኩል እንደ ሳላህ ያለ የክብር ተሸላሚ የነበረው ማህሬዝ በአፍሪካ ዋንጫ ባይሳካለትም ከክለቡ ማንቸስተር ሲቲ ጋር በመሆን ፕሪሚየር ሊግ ማሸነፍ የቻለ ድንቅ ተጫዋች ነው፡፡
ማህሬዝ በፕሪሚየር ሊጉ 11 ግቦች እንዲሁም በሻምፒዮንስ ሊግ 9 ግቦች ማስቆጠር የቻለ ተጫዋች መሆኑም ይታወቃል፡፡
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ይፋ ባደረገው የ10 ተጫዋቾች ዝርዝር ከሶስቱ የእግር ኳስ ኮከቦች በተጨማሪ ሌሎች ተጫዋቾችም አካቷል፡፡
የእጩዎቹ ዝርዝር ውስጥ የሰሜን እና ምዕራብ አፍሪካ ተጨዋቾች እንደሚበዙም ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡
በሆላንድ ኤሪዲቪዚ 21 ጎሎችን ለሻምፒዮኑ አያክስ አምስተርዳም በማስቆጠር ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ያጠናቀቀውን ኮትዲቫራዊው አጥቂ ሰባስቲያን ሃለር ከእጩዎቹ አንዱ ነው።
ቻምፒየንስ ሊግ ግጥሚያዎች በ11 ግቦች ማስቆጠር የቻለው ሃለር፤ በእያንዳንዱ ጨዋታ ግብ በማስቆጠር ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ቀጥሎ በርካታ የጎል ሪከርዶችን መስበር የቻለ አጥቂ ነው።
ከሃላር በተጨማሪ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ያጠናቀቀው ካሜሩናዊው ቪንሴንት አቡባካር፣ ሌላው ካሜሮናዊ ካርል ቶኮ ኢካምቢ፣ ሴኔጋላዊያውያኑ ኤዶዋርድ ሜንዲ እና ካሊዱ ኩሊባ፣ ጊኒያዊው የሊቨርፑል አማካይ ናቢ ኬታ እንዲሁም ሞሮኮው የቀኝ መስመር ተከላካዩ አቻፍ ሃኪሚ በዝርዝሩ ተካተዋል፡፡
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች የሽልማት ስነ ስርዓት እንደፈረንጆቹ ሃምሌ 21 ቀን 2022 በሞሮኮ ዋና ከተማ ራባት ይካሄዳል።