በፈረንጆቹ 2019 በዓለም ዙሪያ የተከሰቱ ዓበይት ፖለቲካዊ ሁነቶች ምን ነበሩ?
በፈረንጆቹ 2019 በዓለም ዙሪያ በርካታ ፖለቲካዊ ሁነቶች ተካሄደዋል፡፡ ከእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ ስልጣን መልቀቅ እስከ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ መከሰስ ድረስ በርካታ አነጋጋሪ ሁነቶች ተከስተዋል፡፡ ሁነቶቹን በዝርዝር ዳሰናቸዋል፡፡
የቴሬዛ ሜይ ከስልጣን መልቀቅ
የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚንስትር ተሬዛ ሜይ እ.ኤ.አ. በሰኔ ወር 2019 ከስልጣን ለቀዋል፡፡ የእንግሊዝ ህዝብ ከአውሮፓ ህብረት ለመነጠል ያሳለፈውን ህዝበዉሳኔ ተከትሎ ወደ ስልጣን የመጡት ሜይ ከህብረቱ ጋር ተደራድረው ሀገሪቱን ከህብረቱ ማውጣት ባለመቻላቸው ተጸጽተዋል፡፡ ቴሬዛ ሜይን ተከትሎ ስልጣን የያዙት ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን የመነጠሉን ድርድር እንዲያሳኩትና ህዝበዉሳኔውንለማሳካት እንዲገፉበት መክረዉ ነበር፡፡
ፕሬዘዳንት ትራምፕ እንዲከሰሱ ኮንግረሱ ማጽደቁ
እ.ኤ.አ በታህሳስ ወር 2019 ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ተወካዮች ምክርቤት እንዲከሰሱ ከተወሰነባቸው ፕሬዘዳንቶች መካካል ሶስተኛ በመሆን በታሪክ ተመዝግበዋል፡፡ ፕሬዘዳንቱ ኢ-መደበኛ መንዶችን ተጠቅመው በዩክሬኑ ፕሬዘዳንት ቮሎድሚር ዘለንሰኪ ላይ ግፈት በማሳደር እ.ኤ.አ በ2020 በሚካሄደው ምርጫ የሚቀናቀኗቸውን ጆ ባይደንን የሙስና ምርመራ እንዲካሄድባቸው ማግባባታቸው ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም በሚል ነው ክሱ የጸደቀው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዘዳንቱ በጆ ባይደን ላይ የሙስና ምርመራ ይፋ እንዲደረግ 400 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት አቅደዋል በሚል በዲሞክራቶች ተጠርጥረውም ነበር፡፡
የአይኤስ አይኤስ መሪ አቡበከር አልባግዳዲ በአሜሪካ ዘመቻ መገደል
በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው የአይኤስአይኤስ መሪ አቡበከር አልባግዳዲ በአሜሪካ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ በሰሜናዊ ሶሪያ የተገደለው እ.ኤ.አ. በጥቅምት 2019 ነበር፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳነት ዶናልድ ትራምፕ “የአለም ቁጥር አንድ አሸባሪው አቡበከር አልባግዳዲን ወደ ፍትህ አምጥተነዋል፤ አልባግዳዲ ተገድሏል” በማላት የድል ዜናውን ለአለም አብስረው ነበር፡፡ የጨካኙና የችግር ፈጣሪው ድርጅት መስራችና መሪ የፈሪ ሞት መሞቱን ፕሬዘዳነቱ ገልጸው ነበር፡፡ አሜሪካ አልባግዳዲን ለአመታት ስትፈልገው የነበረ ሲሆን የሱን መያዝ እንደ ዋነኛ የደህንንት አጀንዳ አድርጋው ነበር፡፡ አልባግዳዲን ለመግደል በምሽት የተካሄደው ልዩ ዘመቻ የተሳካ እንደነበረና ለስኬቱም አሜሪካ ዘመቻውን የመሩትን ወታደሮቿን፣ የአየር ክልል የፈቀዱላትን ቱርክና ሩሲያን አመስግናለች፡፡
ሁለቱ የፕሬዘዳንት ትራምፕና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ውይይቶች
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆን ኡንና የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሀኖይ ከተማ በቬትናም በየካቲት ወር መክረው ነበር፡፡ ሁለቱ መሪዎች በሴሜን ኮሪያ የኑክሌር ማብላላትና ይህን ተከትሎ አሜሪካ በሀገሪቱ ላይ በጣለችው ማእቀብ ዙሪያ ተወያይተውም ነበር፤ ነግር ግን ስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው ስብሰባው በአጭሩ መቋረጡ የሚታወስ ነው፡፡ ሁለተኛውና ያልተጠበቀው ስብስባ ደግሞ ፕሬዘዳንት ትራምፕ በጂ20 ሀገራት ስብሰባ መልስ ከደቡብ ኮሪያው ፕሬዘዳንት ሙን ጃኢን ጋር በመሆን ዲሚሊታራይዝድ ዞን ውስጥ ከ ኪም ጆን ኡን ጋር ውይይት አካሂደው ነበር፡፡ በዚህም ፕሬዘዳነት ትራምፕ ስልጣን ላይ እያለ የሰሜን ኮሪያን ምድር የረገጠ የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት መሆን ችሏል፡፡
ናሬንድራ ሞዲ የህንድ ምርጫ 2019 ማሸነፋቸው
የሂንዱ ናሽናሊሰት ፓርቲን በመወከል ሲወዳደሩ የነበሩት የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እ.ኤ.አ. በግቦት ወር 2019 የህድን ምርጫ አሸንፈዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በድጋሚ መመረጥ በአለም ላይ ከአሜሪካ እስካ ብራዚልና ጣሊያን ድረስ ያሉ ቀኝ አክራሪዎች በስደተኝነትና በመከላከያ ዙሪያ በያዙት አቋም ምክንያት ተቀባይነታቸው እየጨመረ መምጣቱን እንደሚያሳይ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ በሞዲ የሚመራ ባህራቲያ ጃናታ ፓርቲ ከ542 የታችኛው የተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ ድምጽ በማግኘት ነበር ማሸነፍ የቻለው፡፡ ናሬንድራ ሞዲ ምርጫውን ካሸነፉ በኃላ በህንድ ስር የምትገኘውንና ራሰገዝ የነበረችውን የካሽሚር ግዛት የራስ ገዝነትን ስልጣን በመግፈፋቸው በግዛቷ ውስጥ ከሚኖረው ህዝብና ከጎረቤት ፓኪስታን ጠንካራ ተቃውሞ እያስተናገደች ትገኛለች፡፡
ፕሬዘዳንት ሙሃመድ ቡሃሪ የምርጫ በጠባብ ውጤት ማሸነፋቸው
አፍሪካ በ200 ሚሊየን ህዝብ ቁጥር ቀዳሚ የሆነችው ናይጀሪያ ፕሬዘዳንት ሙሃመድ ቡሃሪ በድጋሚ ለአራት አመት እንዲመ መመረጣቸው በአፍሪካ ትልቅ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ፕሬዘዳንት ሙሃመድ ቡሃሪ እ.ኤ.አ. በየካቲት ወር 2019 የተካሄደውን ምርጫ ዋና ተቀናቃኛቸውን የቀድሞውን ምክትል ፕሬዘዳንት አቲኩ አቡበከርን አሸነፉ፡፡ የመራጮች ተሳትፎ 35.6 ፐርሰንት ነበር በተባለው ምርጫ የፒፕልስ ዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪው አቲኩ አቡበከር ውጤቱን አልተቀበሉትም ነበር፡፡ ምርጫው በቀን መዘግየትና በአመጽ የታጀበ ነበር፡፡ የቡሃሪ ፓርቲ 15.2 ሚሊዮን ድምጽ ሲያገኝ በተቃራኒው የአቲክ አበበከር ደግሞ 11.3 ሚሊዮን ድምጽ አግኝተው ነበር፡፡