ቱኒዚያ በሊቢያ ጉዳይ ገለልተኛ መሆኗንና የትኛውንም ጥምረት እንደማትደግፍ ገለጸች
ቱኒዚያ በሊቢያ ጉዳይ ገለልተኛ መሆኗንና የትኛውንም ጥምረት እንደማትደግፍ የቱኒሲያ ፕሬዘዳንት ጸ/ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የሊቢያ መንግሰት በሊቢያ ጉዳይ ገለልተኛ እና የትኛውንም ጥምረት አይቀላቀልም ያለው መግለጫው ቱኒዚያ ሊቢያ ዉስጥ የቱርክን ጎራ ተቀላቀለች የሚለው መግላጫ እንዳሳዘነውም ገልጿል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ጸ/ቤቱ የቱርኩ ፕሬዘዳንት ሪሴፕ ታይፕ ኤርዶሀን መግለጫ ከቱኒሲያው ፕሬዘዳንት ቃይስ ሰይድ ጋር የተወያዩባቸውን ጉዳዮች ይዘት አያንጸባርቅም ብሏል፡፡
የቱኒዚያ ፕሬዘዳንት ጸ/ቤት የሚዲያ ኃላፊ ረቺዳ ኢል-ነፈር ቱኒሲያ በሊቢያ ጉዳይ ገለልተኛ የሆነ መርህ እንደምትከተልና፣ ከሁሉም አካል እርቀቷን እንደምትጠብቅና ከየትኛውም ጥምረት ጋር እንደማትቀላቀል ገልጸዋል፡፡
ኃላፊው ረቺዳ ኢል-ነፈር “ለሊቢያ ደም መፋሰስ ሰላማው መፍትሄ እንዲመጣ ጥሪ እናቀርባለን” ብለዋል፡፡