የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒት በቅርቡ መመረት ይጀምራል ተባለ
የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒትን ለማምረት ላለፉት 50 ዓመታት ሙከራ ሲደረግ ቆይቷል
መድሃኒቱን ለማምረት ኩባያዎች መድሃኒቱ አትራፊ አይሆንም የሚል ዕምነት መያዛቸው እና ፈንድ መጥፋት ጥረቱ እንዳይሳካ ያደረጉ ምክንያቶች ናቸው
የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒት በቅርቡ መመረት ይጀምራል ተባለ፡፡
የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒትን ለማምረት ላለፉት 50 ዓመታ የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡
ይሁንና እስካሁን ድረስ አንድም የወንዶች እርግዝና መድሃኒት ማምረት ያልተቻለ ሲሆን የተደረጉ ጥረቶች አሁን ላይ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡
እንደ ሲቢኤስ ዘገባ ከሆነ የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒትን ለማምረት የተለያዩ ኩባንያዎች በሙከራ ለይ ሲሆኑ በክትባት መልኩ እና በሌሎች መልኩ የሚሰጡ መድሃኒቶችን ለማምረት ሙከራዎች እየተካሄዱ ናቸው፡፡
እየተደረጉ ካሉ የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒቶች መካከል በጄል መልክ ክንድ ላይ የሚቀባው መድሃኒት አንዱ ነው፡፡
በአሜሪካ ብሔራዊ የወሊድ መከላከያ ኢንስቲትዩት በኩል እየተደረገ ያለው ይህ ጄል መሳይ የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒት የመጀመሪያውን እና ሁለተኛውን ደረጃ ሙከራ ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡
የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል 99 በመቶ ውጤታማ ሆኗል ተባለ
ይህ ጄል የወንዶችን የዘር ፈሳሽ መጠን በመቀነስ እርግዝና እንዳይፈጠር የሚያደርግ ነው የተባለ ሲሆን በ222 በጎ ፈቃደኛ ወንዶች ላይ ተሞክሮ እስካሁን ውጤታማ ሆኗል ተብሏል፡፡
ሌሎች ተቋማትም የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒቶችን ለማምረት ጥረቶች ላይ ናቸው የተባለ ሲሆን ከሆርሞን ጋር የማይገናኙ የህክምና ቁሳቁሶችን ለማምረትም ተመሳሳይ ተቋማት የመጨረሻ ደረጃዎች ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
እስካሁን በዓለማችን የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒት ለማምረት የተመዘገበ ህጋዊ ተቋም የሌለ ሲሆን በሙከራ ለይ ያሉ ተቋማት ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ መድሃኒቶችን ለማምረት ፈቃድ ለማግኘት እንደሚያመለክቱ አስታውቀዋል፡፡