የተቃዋሚው ኤም-5 ቡዱን መሪው ቾጉኤል ኮካላ ማይጋ የማሊ ጠቅላይ ሚኒሰትር ሆነው ተሾሟል
በዘጠኝ ወራት ውስጥ ሁለት መፈንቅለ መንግስትን ያስተናገደችው ማሊ በተቋቋመው አዲስ የሽግግር መንግስት አማካኝነት አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰይመች፡፡
በዚህም ቾጉኤል ኮካላ ማይጋ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በጊዜያዊ የማሊፕሬዝዳንት ኮሎኔል አሲሚ ጎይታ በዛሬው እለት መሾማቸውን ነው የፈረንሳይ የዜና ወኪል /ኤ.ኤፍ.ፒ/ ዘግቧል፡፡
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒሰትር ቾጉኤል ኮካላ ማይጋ ባለፈው ዓመት ሰኔ-5 የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኬታን ከስልጣን ለማውረድ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የተሳተፈውን ኤም-5 በመባል የሚታወቀው የአርበኞች ቡድን እንቅስቃሴ መሪ ናቸው።
የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒሰትር ቾጉኤል ኮካላ ማይጋ ሹመት በሰፊው የሚጠበቅ ነበርም ነው የተባለው፡፡
በሙስና ድርጊት ተዘፍቀዋል በሚል የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎችን ተከትሎ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኬይታ በኮሎኔል አሲሚ ጎይታ በሚመራ ወጣት የጦር መኮንኖች ቡድን መገደላቸው የሚታወስ ነው ፡፡
ግንቦት 24 የተደረገው መፈንቅለ መንግስት በአንዳንድ ሲቪሎች ሳይቀር የተደገፈ እንደነበርም ይነሳል፡፡
ጎይታ “ትርምስ” ነው ብሎ በጠራው ሁኔታ ጣልቃ ለመግባት መገደዱን መናገሩንም የሚታወስ ነው፡፡
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከተለያዩ ኃይሎች ጋር ሰፊ ምክክር እንደሚያካሂዱም ጎይታ ተናግረዋል፡፡