ልዩልዩ
የንግስት ኤልዛቤጥ ምርኩዝ ነው በማለት ለመሸጥ የሞከረ ግለሰብ ተቀጣ
ግለሰቡ በማጭበርበር ወንጀል በሳውዝሀምፕተን ማግስትሬት ፍርድ ቤት ለ12 ወራት ቁጥጥር እንዲደረግበት ወስኟል
ግለሰቡ ፖሊስ እየተከታተለው እንደሆነ ከማወቁ እና ከመሰረዙ በፊት ኢባይ ላይ ያቀረበው ጨረታ 686 ዶላር ደርሶ እንደነበር አቃቤ ህግ ገልጿል
የንግስት ኤልዛቤጥ ምርኩስ ነው በማለት ለመሸጥ የሞከረ ግለሰብ ተቀጣ።
የሟቿ ንግስት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ ምርኩስ ነው በማለት ለመሸጥ የሞከረ ግለሰብ በማጭበርበር ወንጀል ቅጣት ተላለፈበት።
የ26 አመቱ ወጣት የንግስት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ ምርኩዝ ነው በማለት ኢባየሮችን ለማጭበርበር በመሞከሩ መቀጣቱን ኤፒ ዘግቧል።
በደቡብ እንግሊዝ ሀምፕሻየር ነዋሪ የሆነው ድሩ ማርሻል የተባለው ግለሰብ ከምርኩዙ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ለካንሰር ጥናት ይውላል ብሎ ነበር።
ግለሰቡ ፖሊስ እየተከታተለው እንደሆነ ከማወቁ እና ከመሰረዙ በፊት ኢባይ ላይ ያቀረበው ጨረታ 686 ዶላር ደርሶ እንደነበር አቃቤ ህግ ገልጿል።
ግለሰቡ በማጭበርበር ወንጀል በሳውዝሀምፕተን ማግስትሬት ፍርድ ቤት ለ12 ወራት ቁጥጥር እንዲደረግበት ወስኟል።
አቃቤ ህጓ እንደገለጹት ዱሩ ማርሻል ከስግብግብ ፍላጎቱ በመነሳት የንግስት ኤልዛቤጥን ሞት ተጠቀሞ የውሽት የበጎ አድራጎት ጨረታ ለማዘጋጀት ሞክሯል።
አቃቤ ህጓ በመጨረሻም የግለሰቡ የማጭበርበር ፍላጎትም ከሽፏል ብለዋል።