ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በልዑሉ ህልፈተ ህይወት “ታላቅ ሀዘን” እንደተሰማቸው ገልጸዋል
የእንግሊዟ ንገስት ኤልሳቤጥ ባለቤት የሆኑት ልዑል ፊሊፕ በ99 ዓመታቸው ህይወታቸው ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል።የቤኪንግሃም ቤተመንግስት “ንግስት የምትወደው ባለቤቷ የልዑል ፊሊፕ ህይወት ማለፉን በጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል ሲል አስታውቋል፡፡
ልዑሉ ዛሬ ጠዋት በዊንሶር ቤተመንግስት ማረፋቸው ነው የተገለጸው ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በልዑሉ ህልፈተ ህይወት “ታላቅ ሀዘን” እንደተሰማቸው የገለጹ ሲሆን ፣ “የንጉሳውያን ቤተሰብ እና ንጉሳዊ ስርዓት ለሀገራችን ሚዛናዊነትና ደስታ የማይታበል ወሳኝ ተቋም ሆኖ እንዲቀጥል በማድረግ አስተዋጽኦ አበርክተዋል” ብለዋል ፡፡
ልዑል ፊሊፕ እና ንግስት ኤልሳቤጥ በፈረንጆቹ 1974 ዓመት ተጋብተው 4 ልጆች እና 8 የልጅ ልጆች አሏቸው። ልኡል ፊሊፕ ከ2017 ጀምሮ ከቤኪንግሀም ቤተ መንግስት ወጥተው ከአደባባይ ቦታዎች ርቀው ቆይተው ነበር።