ስፖርት
በማንቹሪያን ደርቢ ዩናይትድ 2 ለ በሆነ ውጤት አሸነፈ
የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን እስከ 88ኛው ደቂቃ መምራት ቢችልም በሁለት ደቂቃ ልዩነት ግብ አስተናግዷል
ካለፉት 11 ጨዋታዎች አንድ ጨዋታ ብቻ ያሸነፈው ሲቲ የውጤት ቀውስ ቀጥሏል
የማንቸስተር ደርቢ በዩናይትድ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
በኢትሃድ በተካሄደው ፍልሚያ ሲቲ ጆሽኮ ግቫርዲዮል በ36ኛው ደቂቃ ባስቆጥራት ጎል ሲመራ ቆይቷል።
ቀያይ ሰይጣኖቹ በ88ኛው ደቂቃ ያገኙትን የፍጹም ቅጣት ምት ብሩኖ ፈርናንዴዝ ወደ ጎል ቀይሮ አቻ አድርጓል።
ከአቻነቷ ጎል በሁለት ደቂቃ ልዩነት አማድ ዲያሎ ያስቆጠራት ጎል የሩበን አሞሪም ቡድንን
ውጤቱ ከ7 አመታት በላይ በሲቲ ከነበራቸው ቆይታ መጥፎውን ጊዜ እያሳለፉ በሚገኙት ፔፕ ጋርድዮላ ላይ ጫናው እንዲበረታ አድርጓል።
በአንጻሩ የዩናይትድ ደጋፊዎች በፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ሩበር አሞሪም ተስፋ እንዲጥሉ አድርጓል።
ማንችስተር ዩናይትድ ከሲቲ ጋር ከተገናኝባቸው ያለፉት ስድስት ጨዋታዎች መካከል በአምስቱ ተሸንፏል።
ቀያይ ሰይጣኖቹ በኢትሀድ ስታድየም ባደረጓቸው 3 ጨዋታዎች በድምር ውጤት 13 ለ 5 መሸነፋቸውንም አሃዞች ያመላክታል፡፡
በዛሬው ጨዋታም ከአርሰናል በተጨማሪ በእንግሊዝ ቡድን ለብዙ ጊዜ በተከታታይ በመሸነፍ ሌላ ጥቁር ታሪክ ያስመዘግባሉ ቢባልም ዩናይትድ ድል አድርጓል።፡