ተጠባቂው የማንችስተር ደርቢ ጨዋታ በሲቲ የበላይነት ተጠናቀቀ
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን አርሰናል በ21 ነጥቦች ሲመራ ማንችስተር ሲቲ በ20 ነጥቦች በ2ኛ፤ ቶትንሀም በ17 ነጥቦች 3ኛ ላይ ይገኛሉ
በኢትሀድ ስታድየም በተካደው ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ማቸስተር ዩናይትድን 6ለ3 አሸንፏል
ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የስምንተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ተካሂደዋል።
በዛሬው ዕለትም የአንድ ከተማ ተቀናቃኞቹ ማንችስተር ሲቲ እና ማንችስትር ዩናይትድ እግር ኳስ ክለቦች ውድድራቸው አካሂደዋል።
ይህ ጨዋታ በኢትሀድ ስታድየም የተካሄደ ሲሆን ባለሜዳው ማንችስተር ሲቲ ዩናይትድን 6ለ3 አሸንፏል።
ማንችስተር ሲቲ ከጨዋታ የበላይነት ጋር ባሸነፈበት ጨዋታ ጎሎቹን አዲሱ ፈራሚ አርሊንድ ሀላንድ እና ፊል ፎደን እያንዳንዳቸው ሶስት ሶስት ጎል አስቆትረው ሀትሪክ ሰርተዋል።
አዲሱ ፈራሚ አንቶኒ እንድ እንዲሁም ማርሺያል ሁለት ጎሎችን ቢያስቆጥሩም ማንችስተር ዩናይትድን ከሽንፈት አልታደጉትም።
ሁለቱ ክለቦች እስካሁን 187 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን ማንችስተር ዩናይትድ 77 ጨዋታዎች ሲያሸንፍ ሲቲ ደግሞ 57 ጨዋታዎችን ሲያሸንፍ 53 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን የከተማ ተቀናቃኙ የሆነው ቶትንሀምን 3:1 ያሸነፈው አርሰናል በ21 ነጥቦች ሲመራ ማንችስተር ሲቲ በ20 ነጥቦች በሁለተኝነት እንዲሁም ቶትንሀም ሆትስፐር በ17 ነጥቦች በሶስተኛነት እየመሩ ይገኛሉ።
ሌይስተር እስካሁን አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ በደረጃ ሰንጠርዡ ላይ በ20ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ አዲስ አዳጊው ኖቲንግሀም ፎረስት በአራት ነጥብ እንዲሁም ወልቭስ በ6 ነጥብ በ18 እና 19ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።