ቤልጂዬም ለተከታታይ 4ኛ ጊዜ ቀዳሚ በሆነችበት የፊፋ የሃገራት የእግር ኳስ የደረጃ ሰንጠረዥ ኢትዮጵያ 137ኛ ሆነች
ከ2018 ጀምሮ የደረጃው አሸናፊ ቤልጂዬም መሆኗ ይታወቃል
ቤልጂዬም የደረጃ ሰንጠረዡ የዘንድሮ አሸናፊ መሆኗን ፊፋ አስታውቋል
ቤልጂዬም የ2021 የዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ፊፋ) ወርሃ ደረጃ አሸናፊ ሆነች፡፡
ቤልጂዬም ከ2018 ጀምሮ ለ4 ተከታታ ዓመታት ነው የደረጃ ሰንጠረዡን በቀዳሚነት ያሸነፈችው፡፡
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በፈረንጆቹ 2020 ከተሄዱ 352 ጨዋታዎች የተሻለ ቁጥር ያለው ውድድር (1116) በብሔራዊ ቡድኖች ደረጃ መካሄዱን ያስታወቀው ፊፋ ደረጃውን በቀዳሚነት ስትመራ የነበረችው ቤልጂዬም አሁንም ባለችበት ቀጥላለች ብሏል፡፡
ብራዚል እና ፈረንሳይ 2ኛ እና 3ኛ በመሆን ተከታዮቹን ደረጃዎች መያዛቸውን ፊፋ አስታውቋል፡፡ እንግሊዝ፣ አርጀንቲና እና ጣልያን ይከተላሉ፡፡
ብዙ መሻሻሎችን አሳይታለች በሚል ያወደሳት ካናዳ 40ኛ ላይ መቀመጧንም ገልጿል፡፡
ኢኳቶሪያል ጊኒ ጥሩ መሻሻሎችን አሳይታለች ከተባለበት አፍሪካ በዓለም አቀፉ የደረጃ ሰንጠረዥ 20ኛ ደረጃን የያዘችው ሴኔጋል ከአፍሪካ የቀዳሚነትን ደረጃ ይዛለች፡፡
ሞሮኮ፣ አልጄሪያ፣ ቱኒዚያ፣ ናይጄሪያ እና ግብጽ ሴኔጋልን ይከተላሉ፡፡
ኢትዮጵያ ምንም ዐይነት መሻሻልን ሳታሳይ ባለፈው ዓመት እንደነበረችው ሁሉ 137ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ ዋልያዎቹ ከአሁን ቀደም ጥሩ መሻሻልን አሳይተዋል ተብሎ ያስመዘገቡት ከፍተኛ ደረጃ 85 ነው፡፡
ኤርትራም ልክ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ ምንም ዐይነት መሻሻል ሳይኖራት 202ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡