በሌባ አይደፈርም የተባለው ቅንጡ መኪና ከተገዛ ከአንድ ቀን በኋላ ተሰረቀ
227 ሺህ ዶላር ወጪ የተደረገበት ይህ መኪና ያለባለቤቱ ፈቃድ እንደማይነዳ ተገልጾ ነበር
በእንግሊዝ የቅንጡ መኪኖች ስርቆት እየጨመረ መምጣቱ ተገልጿል
በሌባ አይደፈርም የተባለው ቅንጡ መኪና ከተገዛ ከአንድ ቀን በኋላ ተሰረቀ፡፡
ጆን የተባለው እንግሊዛዊ ከሰሞኑ ነበር ቅንጡ የተባለውን ሬንጅ ሮቨር መኪና በ227 ሺህ ዶላር የገዛው፡፡ ግለሰቡ ይህን መኪና ለመግዛት ያነሳሳው ድርጅቱ ባራጨው ማስታወቂያ ያለ ባለቤቱ ፈቃድ በፍጹን የማይንቀሳቀስ መኪና መስራቱን አስታውቋል፡፡
በሀገሪቱ በቅንጡ መኪኖች ላይ የሚፈጸም ስርቆት እየጨመረ መምጣቱ ያሳሰበው ይህ መኪና ገዢም ከስርቆት ነጻ የሆነ መኪና በገበያ ላይ ካለ ለምን አልገዛም በሚል ግዢውን እንደፈጸመ ተናግሯል፡፡
ልዩ የደህንነት ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ተሰርቷል የጠባለው ይህ ሬንጅ ሮቨር 2024 ኤስቪ ሞዴል 500 መኪኖችን ብቻ ለገበያ እንዳቀረበም ኩባንያው አስታውቋል ተብሏል፡፡
ይህ እንግሊዛዊውም ሊሰረቅ አይችልም የተባለውን መኪና ስሙ ካልተጠቀሰው ከዚህ ኩባንያ በገዛ በ60 ሰዓት ውስጥ በሌቦች እንደተሰረቀ ለሚዲያዎች ተናግሯል፡፡
መኪናዋ በቆመችበት ቦታ የተቀመጠው የደህንነት ካሜራ ቀርጾ ያስቀረው ምስል ሲታይ ሶስት ሌቦች በቀላሉ መኪናውን አስነስተው ሲሄዱ ያሳያል፡፡
መኪናውን የሰረቁ ሰዎች ቁልፉን ፍለጋ ካሁን አሁን ወደ መኖሪያ ቤቴ አካባቢ ሊመጡ ችላሉ ብዬ ብጠብቅም እስካሁን ይህ አልሀነም ሲል ለዴይሊ ሜይል ተናግሯል፡፡
የማይሰረቅ መኪና ሰርቻለሁ በሚል ማስታወቂያ ያስነገረው ይህ ኩባንያም በደንበኛው ላይ የተከሰተው ነገር ሲነገረው የሰጠው ምላሽ ደግሞ ፈገግ ያሰኛል፡፡
ኩባንያው በዓለማችን ላይ የትኛውም መኪና ከስርቆት ሊጸዳ አይችልም ሲል ለደንበኛው ምላሽ መስጠቱ ተገልጿል፡፡
መኪናው ውድ ተብለው በገበያ ላይ እየተሸጡ ካሉ መኪኖች መካከል አንዱ ሲሆን ጎማው ብቻ ከ10 ሺህ ዶላር በላይ ወጪ ይጠይቃሉ ተብሏል፡፡