ፑቲን “ምእራባውያን በሩሲያ ንብረት ላይ ለፈጸሙት ስርቆት ይቀጣሉ” ሲሉ ዛቱ
የቡድን 7 አባል ሀገራት ካገዱት የሩስያ ገንዘብ 50 ቢሊዮን ዶላር ለዩክሬን እንዲሰጥ ወስነዋል
ፑቲን “የትኛውም ሀገር በአሜሪካና እና በምዕራቡ ዓለም ለመበዝበዝ የተጋለጠ ነው” ብለዋል
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን “ምእራባውያን በሩሲያ ንብረት ላይ ለፈጸሙት ዝርፊያ ያለ ቅጣት አይታለፍም” አሉ።
የቡድን 7 አባል ሀገራት ሩስያ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ካላት እንዳይንቀሳቀስ ከታገደው ገንዘብ 50 ቢሊዮን ዶላር ለዩክሬን በብድር መልክ እንዲሰጥመወሰናቸው ይታወቃል።
አባላቱ የሩስያ ማዕከላዊ ባንክ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ያስቀመጠው 300 ቢሊዮን ዶላር ካስገኘው ወለድ ላይ ነው ገንዘቡ ለኬቭ እንዲሰጣት የወሰኑት።
ይህንን ተከትሎም ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን “በምዕራቡ ዓለም የሩስያ ንብረት ላይ የፈጸሙት ስርቆት ከቅጣት አያመልጡም ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አርብ እለት እንደተናገሩት ምዕራባውያን ሀገራት በውጭ ከታገዱ የሩስያ ንብረቶችን በመጠቀም ለዩክሬን ብድር ለመስጠት ማቀዳቸው ሌብነት ነው ብለዋል።
ፑቲን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት፥ ምዕራባውያን ሞስኮን የያዙበት መንገድ የትኛውም አገር በምዕራቡ ዓለም ተመሳሳይ የንብረት እገዳ ሰለባ ሊሆን እንደሚችል ያሳያል ብለዋል።
“ምንም ምክንያት ቢደረደርም ስርቆት ስርቆት ነው” ያሉት ፑቲን፤ የስርቆት ወንጀል ደግሞ ያለ ቅጣት አይታለፍም ሲሉም ዛቻ የተቀላቀለበት መልእክት አስተላለፈዋል።
አሁን ላይ በተለይም በምእራባውያን ሀገራ ተከማችተው የሚገኙ የሁሉም ሀገራት እና ኩባዎች እና ገንዘቦች እና ንብረቶች በአስተማማኝ ሁኔታ ላይ የለም ያሉት ፑቲን፤ “የትኛውም ሀገር በአሜሪካና እና በምዕራቡ ዓለም ለመበዝበዝ የተጋለጠ ነው” ብለዋል።
ሩሲያ ጦሯን ወደ ዩክሬን መላኳን ተከትሎ ጦርነት ከተጀመረ 843 ቀናት ያስቆጠረ ሲሆን፤ ይህ ጦርነት በሩሲያ ላይ ከስድስት ሺህ በላይ ማዕቀቦች እንዲጣሉባት አድርጓል።
አሜሪካ እና ምዕራባዊያን ሀገራት ከማዕቀቡ ባለፈ የሩሲያ መንግስት እና ባለሀብቶች ንብረት የሆኑ ሁሉንም ሀብቶች እንዳይንቀሳቀሱ ያገዱ ሲሆን ጦርነቱ መቀጠሉን ተከትሎ ዩክሬንን መልሶ ለመገንባት የሩሲያዊያንን ገንዘብ ጥቅም ለማዋል ማቀዳቸው ይታወሳል።
ሩሲያ ከዚ ቀደም በሰጠችው መግለጫ፤ እንዳይንቀሳቀሱ እገድ የተላለፈባቸው የሩሲያዊያን ሀብትን ለዩክሬን መስጠት የሚያስችል ዓለም አቀፍ ህግ እንደሌለ መግለጿ ይታወሳል።
ድርጊቱ ሌላ ዓለም አቀፍ መዘዝ ያስከትላል ስትል በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል አስታውቃም ነበር።