ኤሪክ ቴን ሀግ የወሰኗቸው አዳዲስ ውሳኔዎች እስካሁን ውጤት አላስገኙላቸውም የተባለ ሲሆን የውጤት ቀውሱ በዚሁ ከቀጠለ የመሰናበት እጣ ይጠብቃቸዋል ተብሏል
ማንችስተር በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ስር ምን ይመስላል?
ሰኔ 2014 ዓ.ም ማንችስተር ዩናይትድን በአሰልጣኝነት የተረከቡት ኤሪኪ ቴን ሀግ የ53 ዓመት ባለጸጋ ሆላንዳዊ ናቸው።
ከአሰልጣኝ ፈርጉሰን በኋላ ያለውጤት ያሉት ዩናይትዶች በኤሪክ ቴን ሀግ ከፍተኛ እምነትን አሳድረውም ነበር።
አሰልጣኙ ከብራይተን ጋር ያደረጉትን የመጀመሪያ ጨዋታ በሽንፈት ቢጀምሩም ዓመቱን ሶስተኛ ሆነው ማጠናቀቃቸው እና በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ እንዲሳተፍ ማድረጋቸው በስኬት ተመዝግቦላቸዋል።
አሰልጣኙ በደጋፊዎች እና በክለቡ አመራሮች ይህን ዓመት በተሻለ ውጤት እንደሚያጠንቅቁ እምነት ጥለውባቸዋል።
አጀማመራቸው ያላማረው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ የውጤት ማጣት ቀውሱ በዚሁ ከቀጠለ የመሰናበት እጣ ሊደርሳቸው ይችላል ተብሏል።
አሰልጣኙ ኦልድትራፎርድ ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ 71 ጨዋታዎችን አድርገው በ45ቱ ድል ሲቀናቸው 10 ጨዋታዎችን ተሸንፈዋል። በቀሪዎቹ ጨዋታዎች ደግሞ በአቻነት አጠናቀዋል።
በ2022/23 የውድድር ዓመት የዴቪድ ዴህያ፣ ካስሚሮ እና አጥቂው ራሽፎርድ ጥሩ ብቃት ማሳየታቸው የተሻለ ውጤት ይዘው እንዲያጠናቅቁ መርዳቱን ፕላኔት ስፖርት ዘግቧል።
ዘንድሮ ግን እነዚህ ተጫዋቾች እንደ አምናው በጥሩ ብቃታቸው ላይ አለመሆናቸው፣ የዴቪድ ዴህያ መልቀቅ እና አዲስ ፈራሚ ተጫዋቾች የታሰበውን ያህል ውጤታማ አለመሆናቸው ለቡድኑ የማሸነፍ ስነ ልቦና መውረድ ምክንያቶች እንደሆኑም ተገልጿል።
ይህ በዚህ እንዳለም አሰልጣኙ እንደ ጄዳን ሳንቾ አይነት ተጫዋቾች ጋር የገቡበት ግጭት በቡድኑ ስነ ልቦና ላይ ጉዳት አድርሷልም ተብሏል።
ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ ከተቀናቃኙ ማንችስተር ሲቲን ጨምሮ ከኒውካስትል፣ ኤቨርተን እና ሌሎችም ክለቦች ጋር ከባድ ጨዋታዎች እንደሚፈተን ይጠበቃ