ሮናልዶ ከፍተኛ ጎሉን ለሪያል ማድሪድ ያስቆረ ሲሆን፤ ለማንቸስተር ዩናትድ ያስቆጠራቸው ግቦች ሁለተኛ ላይ ነው
ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግር ኳስ ዘመኑ ያስቆጠራቸው ግቦች 850 መድረሳቸውን አስታወቀ።
ሮናለዶ የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ክለቡ አል ናሰር አል ሃዛምን 5ለ1 ባሸነፈበት ጨዋታ ላይ ነው 850ኛ ጎሉን ከመረብ ያሳረፈው።
ሮናልዶ ከጨዋታው በኋላ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ፤ “ሌላ ድንቅ ብቃት፤ ከአል ናስር ጋር ከፍተኛ መሻሻል እያመጣን ነው” ብሏል። “በእግር ኳስ ዘመን 850ኛ ግብ ላይ ደርሻለው፤ መቁጠሬንም ቀጥያለሁ” ብሏል።
ሮናልዶ ለማን ምን ያክል ግብ ከመረብ አሳረፈ? ዝርዝሩን ከታች ይመልከቱ