የኡጋንዳ ፖሊስ 20 የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎችን አሰረ
በፖሊስ የታሰሩት ኡጋንዳዊያን የአርሰናልን እና ማንችስተር ጨዋታን በመመልከት ላይ እያሉ ነው ተብሏል
አርሰናልን ከማንችስተር ያገናኘው የትናንቱ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በአርሰናል የበላይነት መጠናቀቁ ይታወሳል
የኡጋንዳ ፖሊስ 20 የአርሰናል እግርኳስ ክለብ ደጋፊዎችን አሰረ።
አርሰናልን ከማንችስተር ዩናይትድ ያገናኘው የትናንቱ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በአርሰናል የበላይነት መጠናቀቁ ይታወሳል።
አርሰናል ማንችስተር ዩናይትድን በማሸነፍ መሪነቱን ያጠናከረበትን ይህን ጨዋታ በመመልከት ላይ የነበሩ ኡጋንዳዊያን መታሰራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በኡጋንዳዋ ጅንጃ ተብላ በምትጠራ አነስተና ከተማ አርሰናል ጎል ማስቆጠሩን ተከትሎ ደስታቸውን በመግለጽ ላይ እያሉ በፖሊስ ታስረዋል ተብሏል።
ፖሊስ 20 የሚደርሱ የአርሰናል ደጋፊዎችን ለምን እንዳሰረ እስካሁን ምላሽ አለመስጠቱም ተገልጿል።
ከፖሊስ እስር ለጥቂት የተረፈ አንድ ኡጋንዳዊ የአርሰናል ደጋፊ እንዳለው "ፖሊስ ምን አጥፍተን ሊያስረን እንደፈለገ አልገባንም ጥፋት የሰራን አይመስለኝም ሲል ተናግሯል።
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በትናንትናው ዕለት የተካሄደው የአርሰናል እና ማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታ 3ለ2 መጠናቀቁ ይታወሳል።
አርሰናል ተቀናቃኙ ማንችስተር ዩናይትድን ማሸነፉን ተከትሎ በ50 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል።
የማሸነፊያ ጎሎቹን ኤዲ ኔኪታህ ሁለት ጎል እንዲሁም ቡካዮ ሳካ አንድ ጎል ለአርሰናል አስቆጥረዋል።
ማንችስተርን ከሽንፈት ያልታደጉ ሁለት ጎሎች ማርከስ ራሽፎርድ እና ተከላካዩ ማርቲኔዝ አስቆጥረዋል።