ፖለቲካ
የጋብቻ ምጣኔ በቻይና በታሪክ ዝቅተኛ የሚባለው ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ
የቻይና ባለስለጣናት የጋብቻ መቀነስ ምክንያት የሚመጣው የውልደት ምጣኔ መቀነስ አሳስቧቸዋል
በቻይና ቀለበት የሚያስሩ ጥንዶች ቁጥር እንዲቀንስ በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት የነበረው እግድ አስተዋጽኦ ነበረው
በቻይና የጋብቻ ሁኔታን መመዝገብ ከተጀመረበት ጀምሮ በ2022 በታሪክ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገልጿል።
ባለፉት አስርት አመታት ጋብቻ ቀጣይነት ባለው መልኩ በከፍተኛ መጠን ሲቀንስ እንደነበር ቪኦኤ ዘግቧል።
ባለፈው አመት 6.83 ሚሊዮን ጥንዶች ጋብቻ ለመፈጸም መመዝገባቸውን በቻይና ሲቪል አፌርስ ሚኒስቴር ድረ ገጽ ላይ ያወጣው መረጃ ያመለክታል። ይህ ቁጥር ከቀደመው አመት ጋር ሲነጻጸር የ800ሺ ቅናሽ አሳይቷል።
በቻይና ቀለበት የሚያስሩ ጥንዶች ቁጥር እንዲቀንስ በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት የነበረው እግድ ተጠቃሽ ነው። ብዙዎች በቤታቸው እና በግቢያቸው እንዲቆዩ አሰገድዷቸው ነበር።
የቻይና ባለስለጣናት የጋብቻ መቀነስ ምክንያት የሚመጣው የውልደት ምጣኔ መቀነስ አሳስቧቸዋል።
በ2022 የቻይና ህዝብ ቁጥር በስድስት አሰርት አመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅናሽ አሳይቷል፤ ይህም በኢኮኖሚዋ እና በአለም ላይ ትልቅ አንደምታ ያስከትላል ተብሏል።
የቻይና ውልደት ምጠኔ በ2022 በ1ሺ ሰው 6.77 ውልደት ዝቅተኛ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን በ2021 በ1ሺ ሰው 7.52 ነበር።