የኡጋንዳ ፕሬዝዳት ልጅ ጀነራል ሙሁዚ ኬኒሩጋባ ለአዲሷ የጣሊያን ጠ/ሚኒሰትር የጋብቻ ጥያቄ አቀረቡ
ጀነራል ሙሁዚ ኬኒሩጋባ በትዊተር ገጻቸው ከሚያጋሩት መልእክት ጋር በተያያዘ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል
100 ከብቶችን ጥሎሽ እሰጣለሁ ያሉት ጄነራሉ፤ ጥያቄው ተቀባይነት ካላገኘ “ጣሊያንን እወራለሁ” ብለዋል
የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የበኩር ልጅ ጀነራል ሙሁዚ ኬኒሩጋባ ለቀጣይዋ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የጋብቻ ጥቃቄ ማቅረባቸው ተነግሯል።
ጀነራል ሙሁዚ ኬኒሩጋባ በትዊተር ገጻቸው ላይ በቀልድ መልእክ ባስተላፉት ጽሁፍ ለጋቻ 100 ከብቶችን ጥሎሽ እንደሚሰጡ መጻፋቸውም ተነግሯል።
ጀነራል ሙሁዚ ኬኒሩጋባ ትዊት ማድተረግ የጀመሩት ለቀጣይዋ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ምን ያክል ከብቶችን መስጠት አለብኝ በሚል መጀመራውም ታውቋል።
በመቀጠል ባሰፈሩት ጽሁፍም “ለደፋርነቷ እና ለቅንነቷ ብቻ 100 ከብቶችብ በስጦታ መልክ እሰጣለሁ” የሚል ትዊት አስከትለዋል።
“ጥያቄው እና ስጦታው ተቀባይነት የማያገኝ ከሆነ ግን ጣሊያንን እወራለሁ” ያሉት ጀነራል ሙሁዚ ኬኒሩጋባ ከጣሊያን ጋር ዲፕሎማያዊ ግጭትን ለማቀርት እና የጥያቄውን ምላሽ ለመጠባበቅ በሚል ትዊተራቸው ላይ ያሰፈሩትን ጽፉፍ ወዲያው መንሳታቸው ተገልጿል።
ጀነራል ሙሁዚ ኬኒሩጋባ የ78 ዓመቱን የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሴቪኒን እንደሚተካ በተደጋጋሚ ቢገለጽም ጀነራሉ ግን በማህበራዊ የትስስር ገጾች የሀገሪቱን ዲፕሎማሲ እና ፕሮቶኮል የሚያበላሹ መልዕክቶችን በማጋራት ላይ ናቸው።
ጀነራል ሙሁዚ ኬኒሩጋባ የእሳቸው በሆነውና ሰማያዊ ባጅ ባለው የትዊተር ገጻቸው እሳቸው የሚመሩት ጦር ናይሮቢን ለመቆጣጠር ሁለት ሳምንት በቂ ነው ብለው ነበር።
ከአንድ ወር በፊት በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት ጀነራሉ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች ዙሪያ በተለይም በሰሜን ኢትዮጵያ ስላለው ጦርነት፣ ሰለ ንጉስ ሚኒሊክ እና ሌሎች ጉዳዮች መልዕክታቸውን በትዊተር ገጻቸው በማሰራጨት ላይ መሆናቸውን ከትዊተር ገጻቸው ተመልክተናል።
ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሴቪኒ ልጃቸው ያደረገው ድርጊት ትክክል ባለመሆኑ እና ኬንያዊያን በማስቆጣቱ ምክንያት ይቅርታ ጠይቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ በልጃቸው ያልተገባ የትዊተር መልዕክት ምክንያት ማዘናቸው የተገለጸ ሲሆን ካለበት የምድር ሀይል አዛዥነት ማንሳታቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ አጋርተዋል።