በታዋቂዋ የቡልጋሪያ ጠንቋይ ባባ ቫንጋ ትንበያ መሰረት በአዲሱ 2023 ዓመት ምን ሊከሰት ይችላል?
የቡልጋሪያ ጠንቋይ ባባ ቫንጋ በህይወት እያሉ የዓለማችን ዋና ዋና ክስተቶችን በየዓመቱ ከፋፍለው ተናግረዋል
ቡልጋሪያዊቷ ባባ ቫንጋ በ2023 የኑክሌር ጦር ሊጀመር እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል
በታዋቂዋ ጠንቋይ ባባ ቫንጋ ትንበያ መሰረት በአዲሱ 2023 ዓመት ምን ሊከሰት ይችላል?
በፈረንጆቹ 1911 በቡልጋሪያ የተወለዱት ባባ ቫንጋ በ85 ዓመታቸው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን የዓለማችን ዋና ዋና ክስተቶችን በየዓመቱ ከፋፍለው ምን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ በህይወት እያሉ ተናግረዋል።
በምስራቅ አውሮፓ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑት እኝህ ቡልጋሪያዊት ማየት የተሳናቸው አካል ጉዳተኛ ሲሆኑ ከዚህ በፊት ይፈጸማሉ ተብለው የተናገሯቸው ግምቶች የተወሰኑት ትክክል መሆናቸውን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረትን ስበዋል።
በተለይም የአሜሪካው የአልሻባብ የመንትዮች ህንጻ ላይ የደረሰው የአውሮፕላን አደጋ፣ የሶቪየት ህብረት መፈራረስ፣ ካንሰር የተባለ በሽታ ሰዎችን እንደሚጨርስ፣ የጃፓን ፉኪሺያማ ኑክሌር ማብለያ መፈንዳት እና ሌሎችም እኝህ ቡልጋሪያዊት ይፈጸማሉ ብለው አስቀድመው ከተናገሯቸው አበይት የዓለማችን ክስተቶች መካከል ዋነኞቹ ናቸው።
ባባ ቫንጋ እስከ 2030 ዓመት ድረስ ሊከሰቱ የሚችሉ የዓለማንን አበይት ክስተቶችን የዘረዘሩ ሲሆን በፈረንጆቹ 5079 ላይ የዓለም ፍጻሜ እንደሚሆንም ጠቁመዋል።
ከአንድ ወር በኋላ በሚገባው የፈረንጆቹ 2023 ዓመት የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንደሚተኮስ፣ የመሬት ምህዋር እንደሚቀየር፣የዓለም ቴክኖሎጂ መስተጓጎል፣ የቤተ ሙከራ ገዳይ ቫይረስ ወይም ሰው ሰራሽ ቫይረስ እንደሚከሰት፣ የሰው ልጅ በቤተ ሙከራ ውስጥ እንደሚፈጠር ከዚህ በፊት የተናገሯቸውን ግምቶች ዋቢ አድርገው ብዙሀን መገናኛዎች ዘግበዋል።
መሬት በአየር ንብረት እና በጨረሮች አማካኝነት በሚደርስባት ጫና ምህዋሯን እንደምትቀይር፣ በዚህ ምክንያትም የጸሀይ ብርሃን ሱናሚ እንደሚከሰትም ተንብየዋል።
ረጅም ጊዜ የሚቆይ ጨለማ እና በረዶ በምድር ላይ እንደሚከሰት የተገለጸ ሲሆን ይሄንን ተከትሎም ብዙዎች በሙቀት እና በሌሎች የአየር ንብረት ለውጥ ጫናዎች ህይወታቸውን እንደሚያጡ ተነግሯል።
ከፍተኛ መጠን ያለው የጸሀይ ሀይል ሲከሰትም የዓለም ተግባቦት ቴክኖሎኪዎች ከአገልግሎት ውጪ ይሆናሉ የተባለም ሲሆን ገዳይ የሆነ ቫይረስ በቤተሙከራ ውስጥ እንደሚፈጠር ቫይረሱም ብዙዎችን ሊገድል እንደሚችል የዚች ቡልጋሪያዊት ትንበያ ያስረዳል።
ሌላኛው በዚህ አዲሱ የፈረንጆቹ 2023 ዓመት ይከሰታል የተባለው ክስተት የኑክሌር ጦርነት መጀመር ሲሆን ጦርነቱ ብዙዎችን ሊያውክ እንደሚችል ተገልጿል።