ጎግል በዓመቱ በብዛት የተፈለጉ ቃላቶችን ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በኢትዮያ በብዛት የተፈለጉትም ተካተዋል
ጎግል በመገባደድ ላይ ባለው የፈረንጆቹ 2022 ሰዎች በድረ ገጹ ላይ በመግባት በብዛት የፈረጉትን (ሰርች) ያደረጉትን ቃላቶች ይፋ አድርጓል።
ጎግል በገጹ ላይ በ2022 በብዛት ከተፈለጉ ቃላቶች ውስጥ “ዎርድል” የሚለው የቪዲዮ ጌም መጠሪያ የሚያክለው አልተገኘም ብሏል በሪፖርቱ።
ህንድ ከእንግለ፤ዝ የሚለው ቃልም በጎግል ላይ በመፈለግ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል የተባለ ሲሆን፤ ይህም ሁለቱ ሀገራት በክሪኬት ባላቸው ጨዋታ ምክንያት ነው ተብሏል።
- ጎግል አፋን ኦሮሞና ትግርኛን ጨምሮ 10 በአፍሪካ የሚነገሩ ቋንቋዎችን በትርጉም አገልግሎቱ አካተተ
- የኦሮሚያ ክልል ባህልና እሴትን የሚያሳይ ቋሚ የኦንላይን ኤግዚቢሽን በጎግል ላይ ተከፈተ
ዩክሬን የሚለው ቃልን በዜና ዘርፍ በብዛት የተፈለገ ቃል ነው የተባለ ሲሆን፤ ይህም በተለይም ሀገሪቱ ከሩሲያ ጋር የገባችውን ጦርነት ተከትሎ ነው የዩክሬን መጠሪያ በብዛት ጎግል ላይ ተፈላጊ ቃል ያድረገው።
ንግስት ኤልሳቤጥ፣ የምርጫ ውጤት፣ የሎተሪ እጣ ቁጥር፣ ሞንኪ ፖክስ (የዝንጀሮ ፈንጣጣ)፣ የዓለም ዋንጫ፣ አይፎን 14፣ የህንድ ፕሪምየር ሊግ እንዲሁም ህንድ ከአሜሪካ የሚሉት ቃላትም በብዛት በመፈለግ እስከ 10 ያሉትን ደረጃ ይዘዋል።
በሲኒማው ዓለም በብዛት ከተፈለጉት ውስጥ ደግሞ፤ “ቶፕጋን፣ መርቪክ፣ ዘ ባትማን፣ ላቭ ኤንድ ተንደር” የሚሉ ርእሶች ጎግል ላይ በመፈለግ ቀዳሚ ሆነዋል።
በኢትዮጵያም በዓመቱ በብዛት ጎግልላይ የተፈለጉ ቃላቶችን አሉ ያሉው ደግሞ ስታሲስታ የተባለ ድረ ገጽ ነው።
በኢትዮጵያ በብዛት ጎግል ላይ ከተፈለጉ ቃላቶች ውስጥም ኢትዮጵያ (Ethiopia) የሚለው ቃል ቀዳሚ ነው የተባለ ሲሆን፤ ፌስቡክ (Facebook) እና ኢትዮጵያን (Ethiopian) የሚለው ቃል ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።
ዩ ትዩብ፣ ሚዩዚክ፣ ፕሪምየር ሊግ፣ ትራንስሌት (ትርጉም) ቴልግራም፣ ጂ ሜይል፣ አርሴናል እና ዳወንሎድ የሚሉ ቃላቶችም በብዛት በኢትዮጵያውያን ጎግል ላይ ተፈለጉ ቃላቶች ናቸው ተብሏል።