ትኩረቱን በኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት ላይ ያደረገው "ዘ ፓሽን ኦፍ ክረስት" ፊልም ዳይሬክተር መኖሪያ ቤቱ በእሳት ወደመ
ሜል ጊብሰንን ጨምሮ በርካታ የሆሊውድ ተዋናዮች ቅንጡ መኖሪያ ቤታቸው በሎሳንጀለሱ እሳት ወድሟል
በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ ያጋጠመው እሳት አደጋ የ150 ቢሊዮን ዶላር ንብረቶችን ሲያወድም ከ100 ሺህ በልይ ዜጎችን አፈናቅሏል
ትኩረቱን በኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት ላይ ያደረገው "ዘ ፓሽን ኦፍ ክረስት" ፊልም ዳይሬክተር መኖሪያ ቤቱ በእሳት ወደመ።
በዓለማችን ቁጥር አንድ ልዕለ ሀያል ሀገር በሆነችው አሜሪካ ሎሳንጀለስ ያጋጠመው እሳት አደጋ አሁንም ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር አልቻለም።
ይህ እሳት አደጋ አደጋ ከ100 ሺህ በላይ አሜሪካዊያን ቤታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ምክንያት የሆነ ሲሆን ከ150 ቢሊዮን ዶላር በላይ ንብረትም አውድሟል ተብሏል።
ቤታቸው ከወደመባቸው አሜሪካዊያን መካከልም ትኩረቱን በኢየሱስ ክርስቶስ ምድራዊ ህይወት ላይ ያደረገው "ዘ ፓሽን ኦፍ ክረስት" ድራማ ጸሀፊ እና ደራሲዎች መካከል አንዱ የሆነው ሜል ጊብሰን አንዱ ሆኗል።
ሜል ጊብሰን ቅንጡ መኖሪያ ቤቱ እየወደመ እያለ እሱ ከጆ ሬጋን ፖድካስት ጋር ቃለ መጠይቅ ላይ ነበር ተብሏል
ከሜል ጊብሰን በተጨማሪም በተከታታይ የኦስካር ሽልማቶችን ያሸነፉ የሆሊውድ ፊልም ተዋናዮችም ይገኙበታል።
ፓሪስ ሂልተን፣ ቢሊ ክሪስታል፣ አዳም ብሮዲ፣ ሚሎ ቬንቲሚግሊያ እና ሌሎችም ተዋናዮች ንብረቶቻቸውን በእሳቱ አጥተዋል ሲሎ ሆሊውድ ኒውስ ዘግቧል።
አንድ ሳምንት ያስተናገደው ይህ ከባድ የእሳት አደጋ በፍጥነት የሚዛመት፣ ለመቆጣጠር አዳጋች እና ንፋስ የቀላቀለ መሆኑ ንብረቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያወድም አድርጎታልም ተብሏል።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እሳቱን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው የተባለ ሲሆን አሁንም መኖሪያ ቤቶቻቸውን ለቀው እንዲወጡ የሚነገራቸው ዜጎች እንዳሉም ተገልጿል።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሎስ አንጀለሱን እሳት አደጋ ለመቆጣጠር እና ለተጎጂዎች ድጋፍ እንዲደረግ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ተብሏል።
የሎሳንጀለስ ከተማ ከንቲባ ካረን ባስ በአደጋው የተጎዱ ዜጎችን የጎበኙ ሲሆን በስፍራው ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።
ተመራጩ ዶናልድ ትራምፕ ከንቲባዋ ለተጎጂዎች በቂ ድጋፍ አላደረጉም በሚል የተቹ ሲሆን ስልጣን እንዲለቁም ጠይቀዋል።