በሎስ አንጀለሱ የእሳት አደጋ ቅንጡ ቤቶቻቸው የተቃጠለባቸው የሆሊውድ ተዋናዮች
የኦስካር ሽልማት አሸናፊው ጀምስ ውድን ጨምሮ በርካታ አርቲስቶች ቤታቸውን አጥተዋል
እሳቱ እስካሁን በቁጥር ስር ማዋል ያልተቻለ ሲሆን ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ ንብረት ወድሟል ተብሏል
በሎስ አንጀለሱ የእሳት አደጋ ቅንጡ ቤቶቻቸው የተቃጠለባቸው የሆሊውድ ተዋናዮች
የዓለማችን ቁጥር አንድ ሀይል ሀገር በሆነችው አሜሪካ ያጋጠመው የእሳት አደጋ ሰዎችን እያፈናቀለ እና ንብረት እያወደመ ይገኛል፡፡
የዓለማችን ኪነ ጥበብ ማዕከል ከሆኑት አንዱ የሆነው የሎስ አንጀለሱ ሆሊውድ ተወናዮችን ጨምሮ የከተማዋ ነዋሪዎች ንብረቶች በእሳቱ በመውደም ላይ ናቸው፡፡
በበርካታ ፊልሞች ላይ በመተወን አድናቆትን ያተረፉ የዝነኛው የሆሊውድ ተዋናዮች ቅንጡ ቤቶቻቸው በመውደማቸው ምክንያት ሲያለቅሱ ታይተዋል፡፡
ጀምስ ውድ ከሲኤንኤን ጋር ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ እንባውን መቆጣጠር ባለመቻሉ ቃለ መጠይቁን ያቋረጠ ሲሆን ቤቱ በመውደሙ ልቡ እንደተሰበረ ተናግሯል፡፡
እስካሁን እየወጡ ባለ መረጃዎች መሰረት ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚወጡ ንብረቶች እንደወደሙ ተገልጿል፡፡
የሎሳንጀለስ ከተማ ከንቲባ ወደ ጋና ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት ሰርዘው በእሳት እየወደሙ ያሉ ቦታዎችን የጎበኙ ሲሆን ከነዋሪዎች ተቃውሞ ገጥሟቸዋል፡፡
ጀኒፈር አኒስተን፣ ቶን ሀንክስ፣ ፓሪስ ሂልተን፣ ቢሊ ክሪስታል፣አዳም ሳንድለር እና ሌሎችም አርቲስቶች ቤታቸው ከተቃጠለባቸው የሆሊውድ ተዋናዮች መካከል ናቸው፡፡