1990 እስከ 2024 በርካታ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች የተከሰተባቸው ሀገራት
በ2024 በሬክተር ስኬል በ5 እና ከዛ በላይ የተለኩ ከ1374 ባላይ የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋል።
በታዳጊ ሀገሮች ወይም የግንባታ ህጎች እምብዛም ጥብቅ ባልሆኑባቸው ሀገሮች ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጦች ከፍተኛ የሞት አደጋ ያስከትላሉ
እሳተ ጎመራን ጨምሮ በተለያዩ የመሬት ውስጥ እንቅስቃሴዎች የሚፈጠሩ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች ከቁጥጥር ውጭ የሆኑ እና የከፋ ጉዳት ከሚያስከትሉ ተፈጥሯዊ አደጋዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
የአሜሪካ ብሔራዊ የመሬት መንቀጥቀጥ መረጃ ማዕከል በዓለም ዙሪያ በቀን 55 በአመት ደግሞ 20 ሺህ የሚጠጉ የመሬት መንቀጥቀጦች እንደሚከሰቱ ይገልጻል፡፡
አብዛኞቹ አነስተኛ መጠን ያላቸው እና ጉዳት የማድረስ እድላቸውም ዝቅተኛ ቢሆንም ነገር ግን ጠንከር ያሉ የመሬት መንቀጥቀጦች እንደየቦታው እና ሌሎች ሁኔታዎችን ታሳቢ በማድረግ የሰው ህይወት፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት ሊያስከትሉ ይችላሉ።
በታዳጊ ሀገሮች ወይም የግንባታ ህጎች እምብዛም ጥብቅ ባልሆኑባቸው ሀገሮች ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጦች ከፍተኛ የሞት አደጋ ያስከትላሉ፡፡
ርዕደ መሬት በየአመቱ 60 ሺሕ ለሚጠጉ ሰዎች ሞት ምክንያት ሲሆን 90 በመቶዎቹ ሞቶች የሚመዘገቡት በታዳጊ ሀገራት ነው፡፡
በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2ሺዎቹ ወዲህ በርዕደ መሬት የደረሱ የሞት ጉዳቶችን ብንመለከት፤ በህንድ ውቂያኖስ አቅራቢያ የተከሰተውን 227 ሺህ 898 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውን አደጋ ቀዳሚ ሆኖ እናገኝዋለን፡፡
ከ1900 ወዲህ በአለም 3ተኛው ከፍተኛው እና አደገኛው ርዕደ መሬት ሆኖ የተመዘገበው ይህ አደጋ በሬክተር ስኬል ከ 9.1–9.3 በሆነ መጠን በኢንዶኔዢያ ሱማትራ ምዕራባዊ የባህር ጠረፍ በፈረንጆቹ 2004 የደረሰ ነው፡፡
160 ሺህ ሰዎች የሞቱበት የ2010 የሄይቲ ርዕደ መሬት እንዲሁም በ2023 በቱርክ እና ሶሪያ የተከሰተው ከ60 ሺ በላይ ሰዎች የሞቱበት አደጋ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በ2024 በሬክተር ስኬል በ5 እና ከዛ በላይ የተለኩ ከ1374 ባላይ የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋል።
1990 እስከ 2024 በርካታ የመሬት መንቀጥቀጥ ከተከሰተባቸው ሀገራት መካከል ቻይና በርካታ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጦች እና ሞት ካስተናገዱ ሀገራት መካከል ቀዳሚዋ ነች፡፡
186 ርዕደ መሬቶች ከተከሰቱባት ቻይና ቀጥላ 166 አደጋዎችን በማስተናገድ ኢንዶኔዥያ ስትከተል ኢራን ፣ ጃፓን ፣ ኤሜሪካ እና ቱርክ በተከታታይ ይገኛሉ፡፡