ከኮሮና ወረርሽኝ መከሰት በኃላ የተከበረው የመጀመሪያው የደመራ በዓል
ከኮሮና ወረርሽኝ መከሰት በኃላ የተከበረው የመጀመሪያው የደመራ በዓል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው የመስቀል ዋዜማ ወይም ደመራ በዓል ዘንድሮ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ጥቂት ምእመናን በተሳተፉበት እየተከበረ ይገኛል፡፡
በዓሉ ለወትሮው በተለይ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሲከበር በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን ይታደሙበት ነበር፡፡
የዘንድሮው የደመራ ፕሮግራም ከተለመደው ሰአት ቀደም ብሎ ተጀምሯል፡፡
የበዓሉን ፕሮግራም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቲያስ በጸሎት አስጀምረዋል፡፡ የመስቀል በዓል በመላው ኢትዮጵያ
በአማኞች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል፡፡
የደመራ በዓል መስቀሉን ለማግኘት ንግስት ኢሌኒ ፍላጋ ያስጀመሩበት ሰለሆነ በአማኞች ዘንድ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው ሀይማኖታዊ በዓል ነው፡፡
የደመራ በዓል ከመስቀል አደባባይ ባሻገር ምእመናን በየቤተክርስቲያቱና በቤታቸው ደመራ በመለኮስ ያከብሩታል፡፡
የመስቀል ደመራ በዓል ከሃይማኖታዊ ይዘቱ በተጨማሪ ባሉት ባህላዊ ትእይንቶቹ በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ የመስቀል ደመራ በዓል ተሳታፊዎች ባጅ እንደሚያስፈልጋቸውና በኮሮና ምክንያት ጥቂት ሰው እንደሚሳተፍ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡