ኮሚሽኑ በደረሰው የእሳት አደጋ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን አስታወቀ
ኮሚሽኑ በደረሰው የእሳት አደጋ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን አስታወቀ
ዛሬ 6 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ላይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሲኤም ሲ በደረሰ የእሳት አደጋ 12 ሚሊዮን 856 ሺ 620 ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ አደጋው ከዚህ በላይም ጉዳት ሊያደረስ ይችል እንደነበር ለአል ዐይን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ከ 48 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረትን ከውድመት መታደግ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡
አደጋውን ለመቆጣጠር አራት ሰዓት ከ15 ደቂቃ መፍጀቱን ያነሱት አቶ ጉልላት አምስት የአደጋ ሰራተኞች በሥራ ላይ ሳሉ ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ብለዋል፡፡
ከ70 በላይ የአደጋ መከላከል ሰራተኞችና ከ14 በላይ ከባድ ተሽከርካሪዎች ጥቅም ላይ ውለዋል ተብሏል፡፡