በእርዳታ ከ2ሺ በላይ ሴት የጤና ባለሙያዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ
በእርዳታ ከ2ሺ በላይ ሴት የጤና ባለሙያዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ለሴት የጤና ባለሙያዎች ኮሮናን መከላከል የሚያስችሉ የህክምና ቁሳቆሶች ድጋፍ ማድረጓን አስታወቀች፡፡
በኢትዮጵያ የሀገሪቱ ኤምባሲ ለአል ዐይን በላከው መግለጫ እንደገለጸው 48 ቶን የሚሆኑ የህክምና ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ድጋ አድርጋለች፡፡ ድጋፉም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ሚያግዝ እንደሆነም ነው ኤምባሲው የገለጸው፡፡
በዚህም ከ 2ሺ በላይ ሴት የጤና ባለሙያዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል፡፡ ሴት የጤና ባለሙያዎች በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ከፍተኛውን ድርሻ እንደያዙ ያነሳው ኤምባሲው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት እረፍት የለሽ ሥራን እየሰሩ ናቸው ብሏል፡፡
ዩኤኢ ያደረገችው ድጋፍ ሀገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ጠንካራ ግንኙነት አካል መሆኑም ተገልጿል፡፡ አዲስ አበባና አቡዳቢ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል አዋጭ በሚባሉ መንገዶች ላይ እየተወያዩና ልምድ እየተለዋወጡ መሆኑም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡
ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ኃላፊነት ከመጡ በኋላ ደግሞ ግንኙነቱ በተለየ መልኩ ጠንካራ ስትራቴጂያዊ መሆኑን ሀገራ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡