ሊዮኔል ሜሲ አዲሱን ማሊያ ለብሰው ፎቶግራፋቸው በክለቡ ከተለቀቀ ተጫዋቾች መካከል የለም
ባርሴሎና አዲስ ያስተዋወቀው ማሊያ ክለቡ በአዲሱ የውድድር ዘመን አርጀንቲናዊውን ኮከብ ሊዮኔል ሜሲን ሊያሰናብት ይችላል የሚል ጥርጣሬን አጭሯል።
የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ለአዲሱ የውድድር ዘመን አዲስ ማሊያ ያስተዋወቀ ሲሆን፣ ሆኖም ግን ሊዮኔል ሜሲ አዲሱን ማሊያ ለብሰው ፎቶግራፋቸው በክለቡ ከተለቀቀ ተጫዋቾች መካከል የለም ተብሏል።
የሊዮኔል ሜሲ በፎቶው ላይ አለመካተትም ተጫዋቹ እና ክለቡ ሊለያዩ ይችላሉ የሚለውን ጥርጣሬ ከፍ አድርጎታል።
በተለይም ሜሲ ከባርሴሎና ጋር ያለውን እና በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ከሚገባደደው ኮንትራት ማራዘም ላይ እስካሁን የተባለ ነገር አለመኖሩም ጥርጣሬውን የባሰ አጉልቶታል።
'ሙንዶ ዴፖርቲሾ' የተባለ የካታላን ጋዜጣ በበኩሉ ሜሲ በአዲሱ ማልያ ማስታወቂያ ፎተ ላይ ባለመገኘቱ ብቻ ከክለቡ ጋር ሊለያይ ይችላል የሚለውን አያመለክትም፣ ክስተቱ የተለመደ እና የሚያጋጥም ነው ያለው።
ሜሲ ያልተካተተበት አዲሱ የባርሰየሎና ማሊያ ማስተወቂያ ፎቶ ባሳለፉነው መጋቢት ወር መነሳቱንም ጋዜጣው አስነብቧል።
በሁዋን ላፖርታ የሚመራው ባርሴሎና እስካሁን ለሊዮንል ሜሱ የኮንትራት ውል ለማደስ ጥያቄ አላቀረበለትም ተብሏል።