ክርስቲያኖ ሮናልዶ የአውሮፓ ዋንጫ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አግቢነት ክብረወሰን ባለቤት ሆነ
ሮናልዶ 11 ጎሎችን በማስቆጠር በፈረንሳያዊው ሚሽል ፕላቲኒ በ9 ጎሎች ይዞት የነበረውን ክብረወሰን ሰብሯል
ሮናልዶ ለሀገሩ ባስቆጠራቸው ጎሎች ብዛትም የፖርቹጋል የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ክብረወሰን ባለቤት ነው
ፖርቹጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ የአውሮፓ ዋንጫ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አግቢነት ክብረወሰን በእጁ ማስገባቱ ተነግሯል።
ሮናልዶ በአውሮፓ ዋንጫ ትናንት ምሽት ፖርቹጋል ከሀንጋሪ ጋር ባደረገችው ጨዋታ ላይ 2 ጎሎችን ከመረብ ማሳረፉን ተከትሎ ነው ክብረ ወሰኑን መስበር የቻለው።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአጠቃላይ በአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ 11 ጎሎችን ከመረብ በማሳረፍ ከዚህ ቀደም በፈረንሳያዊው ሚሽል ፕላቲኒ በ9 ጎሎች ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን የሰበረው።
ሮናልዶ ለሀገሩ ፖርቹጋል በአጠቃላይ ያስቆተረው ጎል ብዛት 106 የደረሰ ሲሆን፤ ይህም በከፍተኛ ግብ አግቢነት በ109 ጎሎች ክብረወሰን ከያዘው ኢራናዊው አሊ ደዪስ ጋር ያለውን ልዩነት እንዲያጠብ አስችሎታል።
ሮናልዶ እስካሁን ለሀገሩ ባስቆጠራቸው ጎሎች ብዛትም የፖርቹጋል የምንጊዜም ከፍተኛ ግል አስቆጣሪ ክብረወሰን ባለቤት መሆን ችሏል።
በከዚህ በተጨማሪም በዘንድሮው የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ ላይ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሌሎች ክብረወሰኖችንም በእጁ ማስገባት ችሏል።
ከእነዚህም መውስጥ በ5 የአውሮፓ ዋንጫ ውድድሮች ላይ ሀገሩን ወክሎ በመሳተፍ ብቸኛው የእግር ኳስ ተጫዋች መሆንም ችሏል።እንዲሁም በ5 ተከታታይ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድሮች ላይ ጎሎችን ከመረብ ያሳረፈ የመጀመሪያው ተጫዋች መሆን እንደቻለም ነው ተነገረው።
የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ በ24 ሀገራት ብሄራዊ ቡድኖች መካከል በ11 ከተሞች ካሳለፍነው አርብ ጀምሮ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።