የአልናስሩ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዘንድሮውን ውድድር ያለዋንጫ እንደማያጠናቅቅ ተናግሯል
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሌሎች ተጫዋቾች ወደ ሳዑዲ አረቢያ በመጓዝ የሀገሪቱን የእግር ኳስ ክለቦች እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቀረበ።
ፖርቹጋላዊው እና የቀድሞው የማንችስተር እና ሪያል ማድሪድ ክለቦች አጥቂ የሆነው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከብዙሀን መገናኛዎች ጋር ቆይታ አድርጓል።
ክርስቲያኖ በቃለመጠይቁ ላይ ስለ ዘንድሮው የሳውዲ ሊግ ውድድር፣ ስለዋንጫ፣ በክለቡ ስለሚኖረው ቀጣይ ቆይታ እና ተጫዋች ዝውውር ተናግሯል።
በ200 ሚሊዮን ዩሮ የሁለት ዓመት ከግማሽ ለሳውዲ አረቢያው አልናስር ፊርማውን ያኖረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ካሳለፍነው ጥር ወር ጀምሮ እየተጫወተ ይገኛል።
ክርስቲያኖ በአልናስር ቆይታውም በ16 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 14 ጎሎችን አስቆጥሯል።
የ38 ዓመቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቀጣይ የዝውውር ወራት ተጨማሪ የአውሮፓ ተጫዋቾች አልናስርን እንዲቀላቀሉ እንደሚፈልግም ተናግሯል።
የሮናንዶ የቀድሞ የቡድን አጋሩ ካሪም ቤንዜማ አልናስርን እንዲቀላቀል የ100 ሚሊዮን ዩሮ ጥያቄ መቀበሉ ይታወሳል።
ክርስቲያኖ አክሎም ወደ አልናስር ታዳጊዎች ጀምሮ እስከ አንጋፋ እድሜ ያሉ ተጫዎቾች ክለቡን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።
የሳውዲው አል ሂላል አርጀንቲናዊው እና ለሰባት ጊዜ ባሎንዶር ዋንጫ አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲን ለማስፈረም ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል።
የሳውዲ ሊግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የብዙዎችን ትኩረት በመሳብ ላይ ሲሆን ተቸማሪ አንጋፋ የዓለማችን እግር ኳስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም በትረት ላይ መሆኑ ተገልጿል።