ሰራተኞቹ ለምሳ መግዣ የተመደበላቸውን በጀት ለጥርስ ብሩሽ መግዣ ማዋላቸው ከስራ እንዲሰናበቱ ዳርጓቸዋል
ሜታ ኩባንያ 25 ዶላር ያባከኑ ሰራተኞቹን ከስራ አሰናበተ፡፡
ፌስቡክን ጨምሮ የዋትስ አፕ እና ኢንስታግራም እናት ኩባንያ የሆነው ሜታ ገንዘብ ያላግባብ አባክነዋል ያላቸውን ሰራተኞች ከስራ አሰናብቷል፡፡
ኩባንያው ለሰራተኞቹ ዕለታዊ በጀት ያለው ሲሆን 25 ዶላር ለምሳ፣ 20 ዶላር ለቁርስ እንዲሁም 25 ዶላር ደግሞ ለእራት በጅቷል፡፡
ሰራተኞቹ ይህን የተቀመጠላቸውን በጀት የጥርስ ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ማለትም ጥርስ ብሩሽ እና ሳሙና የገዙ ሰራተኞች ከስራ እንደተባረሩ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የፌስቡክ እናት ሜታ ኩባንያ በአንድ ቀን 20 ቢሊዮን ዶላር ማጣቱ ተገለጸ
ሰራተኞቹ ከበይነ መረብ የምግብ ዴሊቨሪ ድርጅት ምግባቸውን እንዲያዙ እና እንዲመገቡ የተመደበላቸውን በጀት ላልተገባ አገልግሎት አውለዋል በሚል ኩባንያው እርምጃ ወስዷል ተብሏል፡፡
ሰራተኞቹ ከስራ መባረራቸውን ተናግረው የተባረርነው ያለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ነው ሲሉ መናገራቸው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
በአጠቃላይ በጀቱን ያላግባብ ተጠቅመዋል ተብለው ከስራ የተባረሩ ሰራተኞች ቁጥር 30 እንደደረሰም ተገልጿል፡፡
ሜታ ኩባንያ በበኩሉ ከተወሰኑ ሰራተኞች በስተቀር አብዛኞቹ ከስራ የተቀነሱት ኩባንያው ሰራተኞችን ለመቀነስ በየወሰነው መሰረት እንጂ ያላግባብ በጀት ተጠቅመዋል በሚል እንዳልሆነ አስታውቋል፡፡
ከተባረሩ ሰራተኞች በስተቀር የሜታ ኩባንያ የደህንነት መሀንዲሱ እና ወጣቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ ጃን ማንቹን ይገኝበታል፡፡
ሜታ ኩባንያን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ሰራተኞችን እየቀነሱ ሲሆን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በብዛት እየተጠቀሙ መምጣታቸው ደግሞ ሰራተኞቻቸውን እንዲቀንሱ አድርጓቸዋል ተብሏል፡፡