የሩሲያ ኃይሎች ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላትን የዩክሬኗን 'ኒዩ ዮርክ' ከተማ መቆጣጠራቸውን አስታወቁ
ዩክሬን በፈረንጆቹ 2021 ነበር በሶቬት ህብረት ዘመን ኖብጎሮድስኮይ ስትባል የነበረችውን ከተማ ነው 'ኒዩ ዮርክ' ብላ የሰየመቻት
ወደ ሩሲያዋ ኩርስክ ግዛት የገቡት የዩክሬን ኃይሎች ወደ ፊት ለመግፋት ጥረት ቢያደርጉም፣ የሩሲያ ኃይሎች በምስራቅ ማጥቃታቸውን ቀጥለዋል
የሩሲያ ኃይሎች ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላትን የዩክሬኗን 'ኒዩ ዮርክ' ከተማ መቆጣጠራቸውን አስታወቁ።
የሩሲያ ኃይሎች አጠቃላይ የዶኔስክ ግዛትን ለመያዝ በከፈቱት ጠንካራ ዘመቻ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ አላት ያሏትን የሎጂስቲክ ማከማቻ የሆነችውን "የኒዩ ዮርክ" ከተማ መቆጣጠራቸውን አስታውቋል።
ድንገተኛ ጥቃት በመክፈት ወደ ሩሲያዋ ኩርስክ ግዛት የገቡት የዩክሬን ኃይሎች ወደ ፊት ለመግፋት ጥረት ቢያደርጉም፣ የሩሲያ ኃይሎች በምስራቅ ዩክሬን እያደረጉ ያሉትን ጥቃት አጠናክረው ቀጥለዋል።
ዩክሬን በፈረንጆቹ 2021 ነበር በሶቬት ህብረት ዘመን ኖብጎሮድስኮይ ስትባል የነበረችውን ከተማ ነው 'ኒዩ ዮርክ' ብላ የሰየመቻት።
"በሩሲያ ኃይሎች በተወሰደው ጠንካራ እርምጃ ምክንያት በርካታ የጠላት ታዊጊ ቡድኖች ተደምስሰው እና በቶሬስክ ግዛት የነበረ ሰፊ መንደር እና ቁልፍ የሆነችው ኖቭጎሮድስኮይ ነጻ ወጥተዋል" ብሏል የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ።
ከጦርነቱ በፊት ከ10ሺ የማይበልጥ ህዝብ የሚኖርባት ኒዩ ዮርክ ከስሎቫንስክ ጋር የሚያገናኝ የባቡር መስመር የተዘረጋባት እና ሩሲያ ለማያዝ ስትለፈልጋት የነበረች ነች።
የዩክሬን ጦር በትናንትናው እለት ጠዋት ኒዩ ዮርክን ጨምሮ በቶሬስክ ግንባር ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን ገልጾ ነበር። ነገርገን ዩክሬን ከተማ ስለመያዟ እስካሁን ያለችው ነገር የለም።
ባለፈው ሰኞ እለት በሩሲያ የሚደገፉ ባለስልጣን ቭላድሚር ሮጎቭ የሩሲያ ወታደሮች የዩክሬንን ባንዲራ መሬት ላይ ሲጥሉ የሩሲያን ሰንደቅ አላማ ሲሰቅሉ የሚያሳይ ቪዲዮ ለቀዋል።
ሁለት አመት ያለፈው ዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ለማስቆም የተደረጉ ጥረቶች ባለመሳካታቸው ተባብሶ ቀጥሏል።