ሜታ አገልግሎቱን ከማስታወቂያ ውጭ ለሚጠቀሙ ደንበኞቹ ወርሃዊ ክፍያ በግማሽ እንደሚቀንስ ገለጸ
ሜታ ደንበኞች የሚከፍሉትን ወርሃዊ ክፍያ ከ9.99 ዩሮ በግማሽ ዝቅ በማድረግ 5.99 ዩሮ እንደሚያደርገው የሜታ ከፍተኛ ሰራ አስፈጻሚ በዛሬው እለት ተናግረዋል
ሜታ በአውሮፖ ለሚገኙ ደንበኞቹ ከማስታወቂያ ውጭ በክፍያ አገልግሎት ለመስጠት የጀመረው ፕሮግራም በተጠቃሚዎች ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞታል
ሜታ አገልግሎቱን ከማስታወቂያ ውጭ ለሚጠቀሙ ደንበኞቹ የሚያስከፍለውን ወርሃዊ ክፍያ በግማሽ እንደሚቀንስ ገለጸ።
የሜታ ኩባንያ ከደህንነት ተቆጣጣሪዎች ጋር ያደረገውን ውይይት ተከትሎ ፌስቡክን እና ኢንስታግራምን ከማስታወቂያ ውጭ የሚጠቀሙ ደንበኞቹ የሚከፍሉትን ወርሃዊ ክፍያ ከ9.99 ዩሮ በግማሽ ዝቅ በማድረግ 5.99 ዩሮ እንደሚያደርገው የሜታ ከፍተኛ ስራ አስፈጻሚ በዛሬው እለት ተናግረዋል።
ሜታ ይህን ያደረገው ባለፈው ህዳር ወር በአውሮፖ ለሚገኙ ደንበኞቹ ከማስታወቂያ ውጭ በክፍያ አገልግሎት ለመስጠት የጀመረው ፕሮግራም በተጠቃሚዎች ዘንድ ተቃውሞ እየገጠመው ባለበት ወቅት ነው።
ደንበኞች ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ መክፈል አለባቸው የሚለው የሜታ ፖሊሲ ነው በተጠቃሚዎች ዘንድ ቅሬታ የፈጠሰው።
ሜታ ይህን አገልግሎት የጀመረው ዲጂታል ማርኬት አክት ያወጣውን ማስታወቂያ ያለግለሰቦች ፍላጎት ሊደርሳቸው አይገባም የሚለውን ህግ ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑ ገልጿል።
የሜታ የህግ ባለሙያ ቲም ላምብ በአውሮፖ ህብረት ኮሚሽን ቀርቦ "የተጠቃሚዎች ቁጥር እንዲጨምር እንፈልጋለን። በዚህ ምክንያት ለአንድ አካውንት ክፍያውን ከ9.99 ዩሮ በግማሽ ዝቅ በማድረግ 5.99 እና ለተጨማሪ አካውንት ደግሞ 4 ዩሮ እንዲሆን አድርገናል" ብሏል።
ሜታ ክፍያውን ዝቅ እንደሚያደርግ በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ ለተቆጣጣሪዎች የተናገረ ሲሆን አሁን ላይ ከመረጃ ደህንነት ሰዎች ጋር እየተወያየ ይገኛል።