ፌስቡክን የሚያስተዳድረው ሜታ ኩባንያ በርካታ ሰራተኞቹን ሊያሰናብት መሆኑ ተሰምቷል
ሜታ ከነገ ጀምሮ በርካታ ሰራተኞቹን ማሰናበት እንደሚጀምር ነው የተነገረው
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/09/252-202618-whatsapp-image-2025-02-09-at-7.25.54-pm_700x400.jpeg)
አሜሪካን ጨምሮ በአፍሪካ እሲያ እና ሌሎችም አካባቢዎች የሚገኙ ሰራተኞች ከስራቸው ይቀነሳሉ ተብሏል
ፌስቡክን የሚያስተዳረው ሜታ ኩባንያ በርከት ያሉ ሰራተኞቹን ከስራ ሊያሰናብት መሆኑ ተነግሯል።
ሜታ ኩባንያ ሰራተኞቹን ለማሰናበት ውጥን ቢይዝም በምትኩ ሮቦተችን ስራ የሚያለማምዱ ኢንጂነሮች በመቅጠር ተጠምዷል ነው የተባለው።
ከስራቸው የሚሰናቱ ሰራተኞችን ከነገ ጠዋት ጀምሮ ማሳወቅ ይጀመራል የተባለ ሲሆን፤ ከስራቸው የሚሰናበቱ ሰራኞችም አሜሪካን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ናቸው ተብሏል።
በጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን እና ኔዘርላድስ የሚገኙ ሰራተኞች ቅነሳው አይመለከታቸውም የተባለ ሲሆን፤ ምክንያቱ ደግሞ በሀገራ የሚገኝ ህግ ነው ተብሏል።
ሆኖም ግን በአሜሪካን ጨምሮ በአፍሪካ፣ በአውሮፓ፣ በእሲያ ውስጥ የሚገኙ በርካታ የሜታ ሰራተኞች ከነገ ጀምሮ የስራ ውላቸው መቋረጡን የሚያመላክት መልእክት እንደሚደርሳቸው ሮይተርስ በዘገባው አመላክቷል።
በሰራተኛ ቅነሳው ዙሪያ አስተያየት የተጠየቀው የሜታ ኩባንያ ቃል አቀባይ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል ነው የተባለው።
ኩባንያው ከወር በፊት ካሉት አጠቃላይ ሰራተኞች ውስጥ 5 በመቶውን እንደሚቀስን ማሳወቁ የሚታወስ ሲሆን፤ ከስራቸው የሚሰናበቱ ሰራተኞችም ዝቅተኛ አፈጻጸም ያስመዘገቡ እንደሆኑም አሳውቆ ነበር።
ፌስቡክን የሚያስተዳረው ሜታ ኩባንያ ከፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ሰራተኞቹን ከስራ ሲያሰናብት መቆየቱ ይታወሳል።
የፌስቡክ፣ ዋትስአፕ እና ኢንስታግራም እናት ኩባንያ ሜታ በፈርንቹ 2022 ብቻ 11 ሺህ የሚጠጉ ሰራተኞቹን ያሰናበተ ሲሆን፤ በ2023 ደግሞ 10 ሺህ ገደማ ሰራተኞቹን ከስራ ቀንሷል።
ባሳለፍነው የፈረንጆቹ 2024 ላይም ከተፈቀደላቸው እለታዊ በጀት ውጪ 25 ዶላር ያባከኑ 30 ሰራተኞቹን ማሰናበቱም አይዘነጋም።