የፌስቡክ እናት ሜታ ኩባንያ በዚህ ሳምንት በርካታ ሰራተኞቹን ያባርራል
ዌል ስትሪት ጆርናል ኩባንያው መጠነ ሰፊ የስራ ማሰናበቻ እያዘጋጀ ነው ብሏል
የሜታ እርምጃ ከአፕል ኩባንያ የግላዊነት ፖሊሲ ለውጦች ጋር ይያያዛል ተብሏል
የፌስቡክ እናት ኩባንያ ሜታ በዚህ ሳምንት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን ለማሰናበት አቅዷል ሲል ዎል ስትሪት ጆርናል ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎችን ጠቅሶ ዘግቧል።
ሜታ በጥቅምት ወር ደካማ የሩብ ዓመት አፈጻጸም ማስመዝገቡን አሳውቋል። በዚህ ዓመት ከግማሽ ትሪሊዮን ዶላር በላይ ይሆናል የተባለ እሴት እንዳጣም ተናግሯል።
ሮይተርስ እንደዘገበው ተስፋ አስቆራጩ ትንበያ የመጣው ከቀዘቀዘው የአለም ምጣኔ ሀብት እድገት ፣ ከቲክ ቶክ ውድድር እንዲሁም ከአፕል ኩባንያ የግላዊነት ፖሊሲ ለውጦች ጋር ይያያዛል።
የሜታ ዋና ስራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ እንደተናገሩት የሜታቨርስ ኢንቨስትመንቶች ፍሬ ለማፍራት አስር ዓመታት ያህል ጊዜ እንደሚወስዱ ተናግረዋል ።
እስከዚያው ድረስ ወጪን ለመቀነስ ቅጥርን ማገድ፣ መርሃ ግብሮችን መዝጋት አለበት ነው ያሉት።
የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያው በሰኔ ወር የሶፍት ዌር መሐንዲሶችን ለመቅጠር የያዘውን እቅዱን ቢያንስ በ 30 በመቶ ቀንሷል ነውም የባለው።
ዙከርበርግ ሰራተኞቹን የምጣኔ ሀብት ውድቀቱን እንዲያግዙም አስጠንቅቀዋል ።
ማይክሮሶፍት ኮርፖሬሽን፣ ትዊተር እና ስናፕን ጨምሮ በርካታ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከቅርብ ወራት ወዲህ ስራተኞቻቸውን ከስራ እያሰናበቱ ነወ።
አሊያም የዓለም ምጣኔ ሀብት እድገት በከፍተኛ የወለድ ተመኖች ፣የዋጋ ግሽበት እና በኃይል ቀውስ ሳቢያ እየቀነሰ በመምጣቱ ቅጥርን ቀንሰዋል።