በሜክሲኮ የአንድ ቤተ እምነት ጣሪያ ተደርምሶ 10 ሰዎች ሞቱ
40 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል ተብሏል
አደጋው ሲደርስ ሳንታ ከሩዝ ቸርች በተባለው ቤተ እምነት ውስጥ 100 ገደማ ሰዎች ነበሩ
በሰሜን ሜክሲኮ የሚገኝ እንድ ቤተ እምነት ጣጣ ተደርምሶ በትንሽ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።
ሳንታ ክሩዝ በተባለው ቤተ እምነት ላይ በደረሰው የጣሪያ መደርመስ አደጋ ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች በተጨማሪ 40 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሶ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በአደጋው ከሞቱ ሰዎች መካከል ሁለት ህጻናት እንደሚገኙበትም ፖሊስ አስታውቋል።
አደጋው ሲደርስ ሳንታ ከሩዝ ቸርች በተባለው ቤተ እምነት ውስጥ 100 ገደማ ሰዎች ነበሩ ያለው ፖሊስ፤ በአደጋው ሰዓት አማኞችን የማጥመቅ ስነ ስርዓት ሲካሄድ እንደነበረ ተነግሯል።
በተደረመሰው ጣሪያ ስር በርካቶች መውጫ አጥተው ነበር የተባለ ሲሆን፤ ፖሊስ በኋላ ላይ በህይወት ያሉትን የማውጣት ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል።
የሀገሪቱ ቀይ መስቀል ባለስልጣንት በጣሪያው ስር መውጫ አጥተው የሉ ሰዎችን በሙሉ በህይወት ማትፈረ እንደሚቻል ገልጸዋል።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እና የአካባቢው ነዋሪዎችም በፍርስራሽ ውስጥ ያሉትን ለማውጣት እየተረባረቡ መሆኑም ነው የተገለው።