ፖለቲካ
የላቲን አሜሪካ ሃገራት የአውሮፓ ህብረትን መሰል ቀጣናዊ ተቋም እንደሚያስፈልጋቸው የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት ተናገሩ
የኦብራዶር ንግግር የሌሎችን የቀጣናውን መሪዎች ድጋፍ አግኝቷል
ተቋሙ ግንኙነታችንን የበለጠ ለማጠናከር ያግዘናል ብለዋል ፕሬዝዳንት ኦብራዶር
የላቲን አሜሪካ እና ካሪቢያን ሃገራት መሪዎች አውሮፓ ህብረትን መሰል ቀጣናዊ ተቋም ማቋቋም ያስፈልገናል ሲሉ ተናገሩ፡፡
መሪዎቹ ይህን የተናገሩት ሜክሲኮ ባዘጋጀችው የላቲን አሜሪካ እና ካሪቢያን ሃገራት ማህበረሰብ (CELAC) ዓመታዊ ጉባዔ ላይ ነው፡፡
በጉባዔው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የሜክሲኮው ፕሬዝዳንት አንድሬስ ማኑዔል ሎፔዝ ኦብራዶር አውሮፓ ህብረትን መሰል ቀጣናዊ ተቋም ብናቋቁም ግንኙነቶቻችንን የበለጠ ለማጠናከር፣ ለመደጋገፍ እና ችግሮችን በጋራ ለመቋቋም ያግዘናል ብለዋል፡፡
ይህ የፕሬዝዳንት ኦብራዶር ጥሪ በአሜሪካ የሚዘወረውንና መቀመጫውን ዋሽንግተን ያደረገውን የአሜሪካ ሃገራት ድርጅት (OAS) ማዳከምን ታሳቢ ያደረገ ነው እንደ ሮይተርስ ዘገባ፡፡