ዝነኛው የበይነ መረብ መገናኛ ስካይፒ ሊዘጋ ነው ተባለ
ስካይፒ ከ22 ዓመት በፊት ይፋ ሲደረግ ብዙዎች ተገርመው ነበር

ስካይፒን ተጠቅመው ሲደዋወሉ የነበሩ ሰዎች ሊዘጋ ነው በመባሉ ቅር ተሰኝተዋል
ዝነኛው የበይነ መረብ መገናኛ ስካይፒ ሊዘጋ ነው ተባለ፡፡
ስካይፒ የተሰኘው የበይነ መረብ መገናኛ ቴክኖሎጂ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የተደረገው ከ22 ዓመት በፊት በፈረንጆቹ 2003 ላይ ነበር፡፡
ይህ መተግበሪያ ይፋ ሲደረግ ብዙዎች በፈጠራው የተገረሙ ሲሆን ይህን የተረዳው ማይክሮሶፍት ኩባንያ ቴክኖሎጂውን በ8 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገዝቶታል፡፡
ላለፉት ዓመታ ሰዎች የጠራራቁ ቤተሰቦች፣ ባልና ሚስቶች፣ የተነፋፈቁ ፍቅረኛሞች እና የስራ መሪዎች ይህን ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ጉዳያቸውን ፈጽመውበታል፡፡
አገልግሎቱ ከኢንተርኔት ወጪ ባለፈ በነጻ ይሰራ የነበረ ሲሆን ማይክሮሶፍት ኩባንያ ከቀጣዩ ግንቦት ወር ጀምሮ እንደሚዘጋ አስታውቋል፡፡
ማይክሮሶፍት ኩባንያ ከኮምፒውተር እና ላፕቶፕ ጋር የተያያዙ ስራዎችን የሚያቀላጥፉ የዊንዶው ምርቶቹን ሲያዘምን የመጣ ሲሆን ስካይፒ ከለውጦቹ ጋር ተስማሚ ሆኖ እንዲቀጥል ሲያደርግ እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ይሁንና ዊንዶው 11 የተሰኘው የጽሁፍ ማቀላጠፊያ መተግበሪያ ከስካይፒ ጋር ተስማሚ ሆኖ ባለመቀጠሉ አገልግሎቱን ለማቆም መገደዱ ተገልጿል፡፡
በመሆኑን ስካይፒን በመጠቀም የተለያዩ መረጃዎችን ሲጋሩ የቆዩ ተጠቃሚዎች መረጃዎቻቸውን አስቀድመው እንዲያስተካክሉ ሲልም ኩባንያው አሳስቧል፡፡
ማይክሮሶፍት ኩባንያ ቲምስ የተሰኘ ተመሳሳይ መተግበሪያ ያዘጋጀ ሲሆን ስካይፒን ሲጠቀሙ የነበሩ ተጠቃሚዎች ወደ ቲምስ እንዲዞሩም ምክረ ሀሳቡን ለግሷል፡፡
ዋትስ አፕ፣ፌስቡክ እና ሌሎችም የማህበራዊ ትስስር መተግበሪያዎች ከስካይፒ የተሸለ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ለስካይፒ መዳከም ሌላኛው ምክንት ነውም ተብሏል፡፡