ማይክሮሶፍት ባለው አጠቃላይ ዋጋ የዓለም ግዙፉ ኩባንያ ሆነ
ማይክሮሶፍት ባለው አጠቃላይ ዋጋ ከዓለም አንደኛ የሆነው የቅርብ ተቀናቃኞቹን በመብለጥ ነው
ማይክሮሶፍት በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ ዋጋው 3.3 ትሪሊዮን ዩሮ ይገመታል
የማይክሮሶፍት የቅርብ ተቀናቃኞቹን ንቪዲያ እና አፕልን ኩባንያዎችን በመብለጥ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ ዋጋው 3.3 ትሪሊዮን ዩሮ ይገመታል። ይህ የሆነው የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ(ኤአይ) የሚያደርጉት ፉክክር በጨመረበት ወቅት ነው።
ማይክሮሶት የአለም ትልቅ ዋጋ ያለው ኩባንያ ለመሆን የቻለው በአንጀኛው ተቀናቃኙ ከተበለጠ ከቀናት በኋላ መሆኑን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
የኮምፒውተር ችፕ አምራቹ ንቪዲያ የአንደኛነት ቦታውን የለቀቀው በአሜሪካ ያለው አክሲዮን ገበያ በ3.5 በመቶ ዝቅ በማለቱ እና የኩባንያው አጠቃላይ ዋጋ ወደ 3.2 ትሪሊዮን ዩሮ ዝቅ በማለቱ ምክንያት ነው።
የማይክሮሶፍት ዋጋ በትንሹ የቀነሰ ቢሆንም የቀኑን ገበያ 3.3 ትሪሊዮን ዋጋ በመያዝ አጠናቋል ተብሏል።
ቀዳሚ ለመሆን እየተፎካከሩ ያሉት ማይክሮሶፍት፣ ንቪዲያ እና አፕል በዓለም የመጀመሪያው አራት ትሪሊዮን ዋጋ ያለው ኩባንያ ለመሆንም ብርቱ ጥረት እያደረጉ ናቸው።
ንቪዲያ በአጭር ጋዜ ውሰጥ ሊያድግ የቻለው በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ልማቶች ላይ ኢንቨስት ማድረጉ ነው።
ባለፈው ማክሰኞ በነበረው የአክሲዮን ገበያ በ1000 በመቶ በማደጉ፣ የማይክሮሶፍትን አጠቃላይ ዋጋ ወደ 3.3 ትሪሊዮን ከፍ አድርጎታል።
አንዳንጆች ለዋጋው መጨመር የአክሲዮን ዋጋ ጭማሪን ሲጠቅሱ ሌሎች ግን ከፍ ተደርጎ ግምት ተሰጥቶታል የሚሉም አሉ።
ንቫዲያ በአንጻራዊነት ከሌሎች በአጭር ጊዜ ትርፋማ የሆነ ኩባንያ ነው።
የኢንቨስትመንት ባንክ ተንታኝ የሆኑት ዴ.ኤ ዴቪድሰን ንቫዲያ በኤአይ ላይ ኢንቨት በማድረጉ በፍጥነት አድጓል፤ ነገርግን ይህን እድገት ማሰጠበቅ ከባድ ነው ሲሉ ለስካይ ኒውስ ተናግረዋል።