ማይክሮሶፍት 69 ቢሊዮን ዶላር በማውጣት በአይነቱ ልዩ የሆነ ትልቅ የቪዲዮ ጌም ግዥ ፈጽሟል
ማይክሮሶፍት 69 ቢሊዮን ዶላር በማውጣት በአይነቱ ልዩ የሆነ ትልቅ የቪዲዮ ጌም ግዥ መፈጸሙን ሮይተርስ ዘግቧል።
ማይክሮሶፍት በአሜሪካ ውስጥ ካሉ አንቲትረስት ኩባንያዎች ጋር ለሁለት አመት የቆየ ፉክክር በማድረግ ነው "አክቲቬሽን ብሊዛርድ" የተባለውን ኩባንያ መግዛት የቻለው።
እንደዘገባው ከሆነ ማይክሮሶፍት በታሪኩ ውድ እና ትልቅ የሆነው ግዥ በ69 ቢሊዮን ዶላር ፈጽሟል።
ይህ ግዥ በቪዲዮ ጌም ኢንዱሰትሪ ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል ተብሏል።
በስምምነቱ መሰረት፣ ማይክሮሶፍት የገዛው ኩባንያ ተወዳጅ የሆኑ የቪዲዮ ጌም የሚያመርትባቸውን 'ኮል ኦፍ ዘዴይ'፣ 'ዲያብሎ' ፣ 'ኦቨርዎች' እና የመሳሰሉትን ስቱዲዮችን ይረከባል።
ማይክሮሶፍት ከኩባንያው የወረሳቸውን ጌሞች በማጣመር የቪዲዮ ጌም 'ኔትፍሊክስ' የማድረግ አላማ አለው።
የማይክሮሶፍት ተቀናቃኞች፣ ማይክሮሶፍት እያደጉ የመጡትን የቪዲዮ ጌሞች ውድድርን ለማጨናገፍ ሊጠቀምበት ይችላል የሚል ስጋት አንሰተዋል።