በኢትዮጵያ የኮረና ቫይረስ ያለበትን ስድስተኛ ሰው ተገኝ
በኢትዮጵያ የኮረና ቫይረስ ያለበትን ስድስተኛ ሰው ተገኝ
ቫይረሱ የተገኘባት 6ኛ ግለሰብ ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ የመጣች የ 59 ዓመት እንግሊዛዊ ዜግነት ያላት ዲፕሎማት ስትሆን በ መጋቢት 7/2012 ዓ.ም ከሆቴል በተደረገ ጥቆማ ግለሰቧ በምትገኝበት እራሷን አግልላ እንድትቆይ በማድረግ በተደረገላት የላብቶሪ ምርመራ ናሙና ውጤት የኮሮና ቫይረስ መያዟ ተረጋግጧል፡፡
የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከግለሰቧ ጋር ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች የመለየትና የክትትል ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ግለሰቧ በለይቶ የህክምና መስጫ ማዕከል የቅርብ የሕክምና ክትትል እየተደረገላት ትገኛለች፡፡
የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጰያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠርና በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን በቶሎ ለይቶ እርምጃ ለመውሰድና የበሽታውን ስርጭት ለማስቆም እንዲሁም ጉዳቱን ለመቀነስ ጥረት እያደረገ ይገኛልም ብላለች ሚኒስትሯ፡፡
ህብረተሰቡም ይህንን አውቆ በሁኔታዎች ሳይደናገጥ በተረጋጋ መንፈስ የበሽታውን ስርጭት በመግታት የሚቻለውን ሁሉ እንዲያደርግ ዶ/ር ሊያ ጥሪ አቅርበዋል፡፡