ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ሁሉም የየብስ ድንበሮቿ ለሰዎች ዝውውር ዝግ እንዲሆኑ ወሰነች
ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ሁሉም የየብስ ድንበሮቿ ለሰዎች ዝውውር ዝግ እንዲሆኑ ወሰነች
ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ሁሉም የየብስ ድንበሮቿን ለሰዎች ዝውውር ዝግ መደረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ማስታወቃቸውን ኢቲቪ ዘግቧል፡፡
ከሁሉም ሀገራት በአውሮፕላን ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ሰዎች ራሳቸውን ለ14 ቀናት ለይተው እንዲቆዩ መንግስት መወሰኑ ይታወሳል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢያ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል 5 ቢሊዮን ብር መመደቡን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቀጥር 11 ደርሷል፡፡ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ድንበር ከመዝጋት ባለፈ በርካታ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡
መንግስት ትምህርትቤቶች ለ15 ቀናት ዝግ ሆነው እንዲቆዩና ብዙ ህዝብ የሚሳተፍባቸው ስብሰባዎችም እንዲሰረዙ ወስኖ፣ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ ከቫይረሱ ስርጭት ስጋት ጋር በተያያዘ ፍርድቤቶች ከመጋቢት 10-24 በከፊል ዝግ እንደሚሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት አስታውቋል፡፡
የሀይማኖት ተቋማትም ቫይረሱ እንዳይስፋፋ የጤና ባለሙያዎችን ምክር እንዲተገብሩ ለተከታዮቻቸው አስታውቀዋል፡፡
ከቻይና ውሀን ግዛት የተቀሰቀሰው ቫይረሱ እስካሁን ከ14,700 በላይ ለሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ወረርሽን ብሎ የፈረጀው ኮሮና ቫይረሱ እስካሁን ከ341,000 በላይ ሰዎችን ማጥቃት ችሏል፡፡