ምሳውን በመርሳቱ ምክንያት የ 3 ሚሊዮን ዶላር የሎተሪ ሽልማት ያሸነፈው ግለሰብ
ግለሰቡ አሸናፊ ያደረገውን ጨዋታ ያሸነፈው የሚበላ ነገር ለመፈለግ ወደ ግሮሰሪ በገባበት ወቅት ነው
"መቀለድ እወዳለሁ" ያለው ግለሰቡ ሸልማት ማግኘቱን ለባለቤቱ ለማሳመን ትንሽ ጊዜ እንደወሰደበት ገልጿል
በአሜሪካ ሚዚዎሪ ግዛት ነዋሪ የሆነው ግለሰብ ምሳውን በመርሳቱ ምክንያት የጃክፖት ሎተሪ ሽልማት ማሸነፉ ተገለጸ።
ግለሰቡ ምሳውን ከቤቱ መርሳቱን ተከትሎ በተጫወተው የጃክፖት ሎተሪ የሶስት ሚሊዮን ዶላር ሸልማት ማግኘቱን ዩፒአይ ዘግቧል።
ይህ ግለሰብ ባለቤቱ ምሳውን ረስቶ መሄዱን ደውላ ስትነግረው የሚበላ ነገር ለመፈለግ አርኖልድ ውስጥ በቮገል መንገድ ላይ ወደሚገኝ ሹነክስ ግሮሰሪ ወይም ምግብ ቤት ጎራ ማለቱን ለሚዚዎሪ የሎተሪ ባለስልጣናት ተናግሯል።
ግለሰቡ ወደ ምግብ ቤቱ በገባበት ወቅት የሚፋቅ የሎተሪ ጨዋታ ቀልቡን እንደሳበው ገልጿል።
"ብዙ ጊዜ የ30 ዶላር ቲኬት ጨዋታን አልጫወትም። ነገርግን 60 ዶላር ስለነበረኝ እና ከዚህ በፊትም የሚፋቁ ትኬቶችን አሸንፌ ስለማውቅ፣ ለምን አልሞክረውም አልኩ?" ብሏል አሸናፊው።
ግለሰቡ ትኬቶቹን ሲያይ የሶሰት ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ማሸነፉን አረጋግጧል።
"በጣም ደንግጬ ነበር። አሸንፌያለሁ ብዩ አላሰብኩም ነበር"ብሏል።"ከእዚያ ሁሉንም ዜሮዎች አየሁ።"
ግለሰቡ ማሸነፉን ካረጋገጠ በኋላ መጀመሪያ ያደረገው ለሚስቱ መልሶ መደወል ነበር።
"መቀለድ እወዳለሁ" ያለው ግለሰቡ ሸልማት ማግኘቱን ለባለቤቱ ለማሳመን ትንሽ ጊዜ እንደወሰደበት ገልጿል።ግለሰቡ አሸናፊ ያደረገውን ጨዋታ ያሸነፈው የሚበላ ነገር ለመፈለግ ወደ ግሮሰሪ በገባበት ወቅት ነው