የካንሰር ህመምተኛው የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ጃክፖት ሎተሪ ካሸነፉት ሶስት እድለኞች አንዱ ሆነ
ባል እና ሚስቶቹ ከታክስ በኋላ 422 ሚሊዮን ዶላር በእጃቸው ያስገባሉ
የኦሪጎን ሎተሪ እንዳለው ከሆነ ይህ የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ሽልማት በታሪክ አራተኛው ግዙፍ የፖወርቦል ጃክፖት ነው
ስምንት አመታት በካንስር ሲሰቃይ የነበረው ከላኦስ የመጣው ስደተኛ በዚህ ወር የወጣውን የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ጃክፖት ሎተሪ ካሸነፉት ሶስት እድለኞች አንዱ ሆኗል።
ቸንግ "ቻርሊ" ሳይፋን በኦሪጎን ሎተሪ አማካኝነት በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እሱ እና የ37 አመት እድሜ ያላት ባለቤቱ ዱዋንፔን ግማሹን ገንዘብ እንደሚወስዱ እና ቀሪውን ደግሞ ጋደኛው ላይዛ ቻኦ እንደምትወድ አስታውቋል።
ቻኦ አሸናፊ ያደረጋቸውን ትኬት ለመግዛት 100 ዶላር አዋጥታለች።
ባል እና ሚስቶቹ ከታክስ በኋላ 422 ሚሊዮን ዶላር በእጃቸው ያስገባሉ።
"ቤተሰቤን መርዳት እና መታከም እችላለሁ" ያለው ሳይፋን ህመሙን ለመታከም "ጥሩ ዶክተር" እንደሚያገኝ ጨምሮ ገልጿል።
ሁለት ወጣት ልጆች እንዳሉት የገለጸው ሳይፋን የካንሰር ህመምተኛ በመሆኑ"ይህን ሁሉ ገንዘብ ምን አደርገዋለሁ?፤ ምን ያህል ነው የምኖረው?" በሚል ጭንቀት ውስጥ ገብቷል።
ትኬቱን በጋራ ከገዙ በኋላ ቻኦ የትኬቱን ፎቶ "ቢሊየነር ሆነናል" የሚል መልእክት በማያያዝ ለሳይፋን ልካለት ነበር። "ይህ እጣው ከመውጣቱ በፊት ቀልድ ነበር፤ ነገርግን በሚቀጥለው ቀን ማሸነፋቸውን ይናገራል።"
ሳይፋን የማሸነፋቸውን ዜና ሊነግራት ሲደውል የ55ቷ ቻኦ ወደ ስራ በመሄድ ላይ ነበረች፤ "ከዚህ በኋላ መሄድ አይጠበቅብሽም" ነበር ያላት።
በላኦስ የተወለደው ሳይፋን ወደ አሜሪካ በ1994 ከመሰደዱ በፊት በ1987 ወደ ታይላንድ አቅንቶ ነበር።
ሳይፋን ዝርያው መነሻቸውን ደቡብ ቻይና ካደረጉ ሉ ሜይን ከተባሉ የደቡብ እስያ ጎሳዎች የሚመመዝ ሲሆን ቤተሰቦቹ በቬትናም ጦርነት ወቅት ለአሜሪካ ወታደሮች እርዳታ አድርገዋል። ጦርነቱ ካበቃ በኋላ በቀልን የፈሩት ቤተሰቦቹን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የሉ ማይን ጎሳ አባላት ወደ ታይላንድ ከእዚያ ወደ አሜሪካ ሊሰደዱ ችለዋል።
ሳይፋን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በ1996 ያጠናቀቀ ሲሆን በፖርትላንድ ለ30 አመታት ያህል ኖሯል። ለአንድ የኤሮፔስ ኩባንያም የማሽን ባለሙያ ሆኖ ሲሰራ ነበር።
ሎተሪ ሊወጣ ሳምንት ሲቀረው የሎተሪ ቁጥሩን በብጫቂ ወረቀት ላይ ከጻፈ በኋላ በትራሱ ስር አድርጎ መተኛቱን ሳይፋን ይናገራል። "እርዳታ እፈልጋለሁ፤ ለቤተሰቤ ምንም ሳላደርግላቸው መሞት አልፈልግም" በማለት ለማሸነፍ ጸሎት አድርጓል።
የኦሪጎን ሎተሪ እንዳለው ከሆነ ይህ የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ሽልማት በታሪክ አራተኛው ግዙፍ የፖወርቦል ጃክፖት ሲሆን በአሜሪካ ዳክፖት ውድድሮች ደግሞ በግዙፍነቱ ስምንተኛ ነው።
በአሜሪካ ግዙፉ የጃክፖት ሎተሪ በ2022 በካሊፎርኒያ የወጣው 2.4 ቢሊዮን ዶላር ነው።