ሀናን መሀመድ የተባለችው ይህች እንስት የዱባይ ቀረጥ ነጻ ሎተሪን በማሸንፍ ሶተኛዋ ኢትዮጵያዊ ሆናለች
በዱባይ የምትኖረው ኢትዮጵያዊት የአንድ ሚሊዮን ዶላር ሎተሪ አሸነፈች፡፡
የተባበሩት አረብ ኢምሬት የኢኮኖሚ መዲና የሆነችው ዱባይ ወደ ከተማዋ የሚገቡ ጎብኚዎችን ለማበረታታት በሚል በየጊዜው ከቀረጥ ነጻ ሎተሪ አዘጋጅታለች፡፡
በአዲስ ዓመት ላይ የሚወጣው ይህ ሎተሪም አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚያሸልም ሲሆን ኢትዮጵያዊቷ ሀናን መሀመድ አብዱረህማን የተሰኘች እንስት ሽልማቱን እንዳሸነፈች ተገልጿል፡፡
ይሁንና ይህች እድለኛ ሎተሪው እንደደረሳት እስካሁን አላወቀችም የተባለ ሲሆን ሽልማቱን ለመውሰድ እንዳልመጣች ገልፍ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ከኢትዮጵያዊቷ በተጨማሪም ሌላ አንድ ሕንዳዊ አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚያሸልመው ሎተሪ አሸንፏል የተባለ ሲሆን ሽልማቱንም ወስዷል ተብሏል፡፡
ይህን ሽልማት ደጋግሞ በማሸነፍ ሕንዳዊያን ቀዳሚ ሲሆኑ ኢትዮጵያ እስካሁን ሀናንን ጨምሮ ሶስት ዜጎች አሸንፈዋል፡፡
የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ቢሮውን ሊዘጋ እንደሚችል አስጠነቀቀ
ከፈረንጆቹ 1999 ጀምሮ በየዓመቱ የሚዘጋጀው ይህ ሎተሪ ሕንዳዊያን 22 ጊዜ ሎተሪውን አሸንፈዋል ተብሏል፡፡
ይህ ጎብኚዎች ወደ ዱባይ እንዲመጡ ለማበረታታት ታስቦ የተዘጋጀው ይህ ሎተሪ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር ሽልማት በተጨማሪ ቅንጡ ማርቸዲስ ቤንዝ አውቶሞቢል ተሸከርካሪም ያለው ሲሆን ለሌላኛው ሕንዳዊ ወጥቷል፡፡