በዓለም ዙሪያ የተመዘገበ ሞባይል ስልክ ብዛት ከዓለም ህዝብ ቁጥር ማለፉ ተገለፀ
በዓለም ዙሪያ የተመዘገቡ ስልኮች የዓለም ህዝብ ቁጥርን በስንት ይበልጣል?
አሁን ላይ የዓለም ዙሪያ ተመዝግበው ያሉ የሞባይል ስልክ ብዛት ከ8.3 ቢሊየን አልፏል
የሞባይል ስልክ ወደ ዓለማችን ከመጣ ወዲህ ጀምሮ በሰዎች የእለት ተእለት እንቅስቃሴን ጨምሮ በበርካታ ነገሮች ላይ ለውጥ እንዲመጣ ማድረጉ ይታወቃል።
ሞባይል ስልኮች ሰዎች የግል ግንኙነቶችን ከመቀየር ጀምሮ ዓለም በትምህርት፣ በግብይት እና በፖለቲካዊ ክርክሮች ውስጥ የሚሳተፍበትን ሁኔታ ቀይሯል።
የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከእለት እለት እየጨመረ መጥቶ አሁን ላይ በዓለም ዙሪያ የሞባይል ስልክ ብዛት ከህዝብ ብዛት በቁጥር እየበለጠ መምጣቱም መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በዓለም ላይ ያለው የሞባይል ስልክ ባዛት በቁጥር
በዓለም ዙሪያ የተመዘገበ የሞባይል ስልክ ብዛት ከዓለም ህብዝበ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለፈው በፈረንጆቹ 2017 ላይ ሲሆን፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ቁጥሩ በእጥፍ እያደገ መጥቷል።
በቅርብ የወጣ መረጃ እንደሚያሳየውም በዓለም ላይ ያለው የህዝብ ቁጥር 7.98 ቢሊየን ሲሆን፤ በዓለም ዙሪያ የተመዘገቡ የሞባይል ስልኮች መጠን ደግሞ ከ8.3 ቢሊየን አልፏል።
ባደጉት ሀገራት የሞባይል ስልክ ተጠቃሚነት ደረጃ 100 በመቶ የደረሰ ሲሆን፤ በማደግ ለይ ባሉት ሀገራት ደግሞ ከ75 እስከ 79 በመቶ ደርሷል።
እንደ መረጃው ከሆነ በዓለም ዙሪያ ተመዝግበው ካሉ የሞባይል ስልኮች ውስጥ 80 በመቶው ስማርት ስልክ መሆኑም ተመላክቷል።
በዓለም ዙሪያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር
አሁን ላይ በዓለም ዙሪያ ያሉ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር 4.9 ቢሊየን መድረሱን በቅርቡ የቀጣ መረጃ ይጠቁማል።
አሁን አሁን ለስራም ይሁን ለመዝናናት ኢንርኔት ተመራጭ እየሆነ መምጣቱን ተከትሎ የተጠቃሚዎች ቁጥር ለማደጉ በምክንያትነት ይጠቀሳል።
በተለየም የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) መከሰትን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ዓመታት ኢንተርኔት ስራ ለመስራት፣ መማር እና አገልግሎቶችን ማግኘት ወሳኝ እንዲሆን አድርጎታል።
አሁን ላይ ባለው መረጃ ከዓለም ህዝብ 63 በመቶው የኢንተርኔት ተጠቃሚ ሆኗል፤ ይህ አሃዝም ከፈረንጆቹ 2019 ወዲህ የ17 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱም ነው የተገለፀው።
በአፍሪካ፣ በኢሲያ፣ በፓስፊክ እና በሌሎችም በማደግ ላይ ባሉ ሀገራም ቢሆን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር በ20 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱም ነው የተገለጸው።