ሁዋዌይ በየትኛውም የዓለም ክፍል በሳተላይት የሚሰራ ሜት 50 ስማርት ስልክ ይፋ አደረገ
አዲሱ ሜት 50 ስማርት ስልክ ባትሪ ሊዘጋ 1 ፐርሰት እየቀረው 3 ሰዓት መቆየት ይችላል
ሁዋዌይ ሜት 40 ስማርት ስልክን ከለቀቀ ከ2 ዓመት በኋላ ነው ሜት 50 ይፋ የተደረገው
የቻይናው የቴክኖሎጂ ቁሶች አምራች ሁዋዌይ ሜት 50 ስማርት ስልኩን በዛሬው እለት ይፋ ማድረጉ ተነግሯል።
አዲሱ የህዋዌይ ስማርት ስልክ ከዚህ በፊት በስማርት ስልኮች ላይ ያልተለመደ የሳተላይት ኮሙዩኒኬሽን የተገጠመለት መሆኑን ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል።
በዚህም ስማርት ስልኩ ከጂ.ፒ.ኤስ ተመሳሳይነት ባለው በቻይናው ቤይ-ዶው ናቪጌሽን ሳተላይት ሲስትም (BDS) ኔትዎርክ አማኝነት በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚባይል ኔትዎርክ ባይኖርም መስራት ይችላል።
በተጨማሪም አዲሱ ሜት 50 ስማርት ስልክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአሜሪካው የጎግል አንድሮይድ ስማርት ስልክ በመላቀቅ ቻይና በራሷ ባመረተችው አዲስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ የሚቀርብ ይሆናል ነው የተባለው።
አዲሱ የሁዋዌይ ሜት 50 ስማርት ስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ሀርሞኒ የሚባል ሲሆን፤ በተለይም የስልኩን የባትሪ እድሜ ማራዘም ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣ ነው ተብሏል።
ይህም ባትሪው ሊዘጋ 1 ፐርሰት እየቀረው 3 ሰዓት እንደቆይ ማድረግ እንደሚያስችልም ኩባያው አስታውቋል።
አዲሱ የሁዋዌይ ሜት 50 ስማርት ስልክ የባትሪ አቅም 4460 mAh መሆኑን ኩባያው አስታውቋል።
ስማርት ስልኩ ከጀርባው 4 የካሜራ ሌንሶች የተገጠሙለት ሲሆን፤ ሌንሶቹም 50 ሜጋ ፒክስል፣ 13 ሜጋ ፒክሰል እና 12 ሚክስል ናቸው።
ከፊትለፊት አሊያም ሰለፊ ካሜራው ደግሞ 1 ሲሆን፤ የሌንሱ ምስል የማንሳት ጥራትም 13 ሜጋ ፒከስል ነው ተብሏል።
ሁዋዌይ ሜት 40 የተባለ ስማርት ስልክን ከለቀቀ ከ2 ዓመት በኋላ ነው ሜት 50 ስማርት ስልክ ይፋ የተደረገው።
በርካቶቸ ሁዋዌይ ስማርት ስልኩን ይፋ ሳያደርግ ይህን ያክል የቆየው አሜሪካ በኩንያው ላይ በጣለችው ማእቀብ ሳቢያ ሳይሆን እንዳልቀረ ያምናሉ።