በእስራኤል ለልጆች ከሚወጡ ስሞች መካከል "መሐመድ" የሚለው 3ኛ ደረጃን ይዟል ተባለ
ዮሴፍ የሚለው ስም አንደኛ ሲሆን፤ ዳቪድ/ዳዊት የሚለው 2ኛ ደረጃን ይዟል

እስራኤል ከተመሰረተችበት 1948 ጀምሮ በሀሪቱ በስፋት ጥቅም ላይ የዋሉ ስሞችን የሚያሳይ ሪፖርት ወጥቷል
በእስራኤል ለልጆች ከሚወጡ ስሞች መካከል "መሐመድ" የሚለው ሶስተኛ ደረጃን መያዙን ሪፖርት አመለከተ።
እስራኤል እንደ ሀገር ከተመሰረተችበት 1948 ጀምሮ በሀሪቱ በስፋት ጥቅም ላይ የዋሉ ስሞችን የሚያሳይ ሪፖርት የወጣ ሲሆን፤ አስገራሚ እና ያልተጠበቁ ስሞች ተካተውበታል።
የእስራኤል ጋዜጣ "ዬዲዮት አህሮኖት" ይዞት በወጣው ሪፖርት እስራኤል እንደ ሀገር ከተመሰረተችበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ቀዳሚ የሆነው ስም “ዮሴፍ” ነው።
ዴቪድ/ዳዊት የሚለው ስም በሀገሪቱ በስፋት ጥቅም ላይ በመዋል 2ኛ ደረጃን ሲይዝ፤ መሀመድ የሚለው ደግሞ 3ኛ ደረጃን መያዙ ያመለክታል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ መሃመድ የሚለው ስም ለልጆች በመውጣት ቀዳውን ደረጃ እየያዘ መምጣቱንም ሪፖርቶች ያመለክታሉ።
የእስራኤል የስነ ህዝብ እና ኢሚግሬሽን ቢሮ ባሳለፍነው የፈረንቹ 2024 በለቀቀው የስሞች ሪፖርት በሀገሪቱ ለልጆች ከወጡ ስሞች መካከል መሀመድ የሚለው ቀዳሚው መሆኑን አስታውቋል።
በዓመቱ በእስራኤል ከተወለዱ 181 ሺህ ህጻና መካከልም 1 ሺህ 740 ህጻናት መሃመድ የሚል ስም የወጣላቸው ሲሆን፤ ዮሴፍ የሚለው ስም ለ1 ሺህ 201 ልጆች አንዲሁም አዳም የሚለው ስም ደግሞ ለ1 ሺህ 196 ልጆች መውጣቱን ቢሮው አስታውቋል።
በፈረንቹ 2023 በእስራኤል ውስጥ በብዛት ለህጻንት ልጆች ከወጡ ስሞች መካከል መሃመድ ቀዳሚው እንደነበረም ነው የታምስ ኦፍ እስራኤል ዘገባ የሚያመላክተው።
በሴቶች ስም ደግሞ እስራኤል እንደ ሀገር ከተምረተች ወዲህ በስፋት ጥቅም ላይ የዋለ እና ተወዳጅ የሆነ ቀዳሚው ስም “ሳራ” መሆኑን በሪፖርቱ ተመላክቷል።
“ራሄል” የሚለው ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ ሜሪ፣ አስቴር እና ሀና የሚሉ ስሞች ደግሞ ከሶስተኛ እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል ነው የተባለው።
ርብቃ፣ ያኤል፣ ሚካል፣ ታማር፣ እና ሊና በቅደም ተከተላቸው መሰረት እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።